ሥላሴ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
ሥሉስ ቅዱስ
ሥሉሥ ቅዱስ
 

ሥላሴ ማለት ሠለሰ ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፣ ቃሉም የግእዝ ነው። ይህ ቃል የአምላክን አንድነትና ሦስትነትንያመለክታል። የሥላሴ እምነት የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖቶች ዋነኛ መሰረተ ትምህርት ነው። በዚህ ሁናቴ ፈጣሪ አንድላይ በሦስት ቦታዎች ሊኖር ይችላል። ፩) በመሢሕ ይኖራል (ወልድ)፤ ፪) በልባችንን ይኖራል (መንፈስ ቅዱስ)፤ ፫) በማይታይ ሰማያት የትም ቦታ ይኖራል (አብ)።

አትናቴዎስ ሃይማኖታዊ ድንጋጌ መሰረት ሁሉም ዘላለማዊ የሆኑ፣ እያንዳንዳቸው ሁሉን ማድረግ የሚችሉ፣ አንዳቸው ከአንዳቸው የማይበላለጡ፣ ሁሉም አምላክ የሆኑ ሦስት መለኮታዊ አካላት (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) አሉ። ይሁን እንጂ ሦስቱም አንድ አምላክ ናቸው እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም። ስለዚህ ቀኖና የተሰጡ ሌሎች መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ሦስት "አካላት" መለኮታዊው ህልውና የሚገለጥባቸው ሦስት መንገዶች ናቸው እንጂ የተለያዩና ግላዊ ሕልውና ያላቸው "አካላት" አይደሉም። በዚህም ምክንያት አንዳንድ የሥላሴ አማኞች ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ወይም ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ ይሖዋ እንደሆኑ አጥብቀው ያምናሉ። አምላክ አንድ ሲሆን ሶስት ሶስት ሲሆን አንድ ማለት ነው፤ በስም፣ በአካል እነ በግብር ሶስት ሲሆን በህላዌ እና በመለኮት አንድ ነው።

ደግሞ ይዩ፦ የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትየተሰሎንቄ ዐዋጅ

የሥላሴ እምነት ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሥላሴ እምነት ደጋፊዎች ማቴ. ፳፰፡፲፱ ያጠቁማሉ። ሆኖም ተቀራኒ ድምጾች እንደሚሉ ይህ ጥቅስ በኋላ ነበር ወደ ወንጌሉ የተጨመረው። ከዚህ በላይ የሥላሴ ትምህርት የሚቀበሉት አብያተ ክርስትያናት ፪ ቆሮንቶስ ፲፫፡፲፬ እና ፩ ቆሮንቶስ ፲፪፡፬-፮ ሲያመለከቱ፣ ይህ እምነት ከመጀመርያ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ እንደ ተመሠረተ ለማስረዳት ይጣራሉ።

ዳሩ ግን ሌሎች መምህሮች ለነዚህ ነጥቦች ትልቅ ስፍራ አይሠጡም። በእንግሊዝኛ የተጻፈው ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦ «ሥላሴ የሚለው ቃልም ሆነ በግልጽ የተብራራ የሥላሴ መሰረተ ትምህርት በአዲስ ኪዳን ውስጥ አይገኝም። ኢየሱስም ሆነ ተከታዮቹ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን፦ 'እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው' (ዘዳግም ፮፡፬) የሚለውን ለማስተባበል አላሰቡም። . . . የሥላሴ እምነት ቀስ በቀስ የተስፋፋው በበርካታ መቶ ዓመታት ውስጥ ከብዙ ንትርክ በኋላ ነው። . . . የሥላሴ መሰረተ ትምህርት አሁን ያለውን ቅርጽ የያዘው በአራተኛው መቶ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው።» [1]


:
  1. ^ ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ (1976)፣ ማክሮፔድያ፣ ጥራዝ 10፣ ገጽ 126