ደብረ ታቦር (እስራኤል)
Jump to navigation
Jump to search
ደብረ ታቦር (የታቦር ተራራ) | |
---|---|
![]() | |
ከፍታ | 575 ሜትር |
አቀማመጥ | |
አቀማመጥ | አቀማመጥ |
ኬክሮስ እና ኬንትሮስ | 32°41′13.61″N 35°23′25.38″E / 32.6871139°N 35.3903833°ECoordinates: 32°41′13.61″N 35°23′25.38″E / 32.6871139°N 35.3903833°E |
ደብረ ታቦር እስራኤል ውስጥ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በአዲስ ኪዳን ታሪክ መሰረት ሕዋርያት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብ እያዩ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ እንደጸሐይ ያበራበት ቦታ እንዲሁም ሙሴንና ኤልያስን በተዓምር ከሙታን አንስቶ ያሳያቸውበት ቦታ (ማቴ (17:1-6)፤ማርቆስ (9:1-8)፤ ሉቃ (9:28-36)) ነው ተብሎ ይታመናል። ስለሆነም ለደብረ ታቦር (ዓመት በዓል) መሰረት የሆነ ቦታ ነው። ኢትዮጵያም ውስጥ ደብረ ታቦር (ከተማ) የተሰየመው በከተማው ሰሜን የሚገኘው ተራራ የዚህን ኮረብታ ቅርጽ ስለያዘ ነው።
ደብረ ታቦር እስራኤል በመጽሐፈ መሳፍንት 4 መሠረት የምድያምን ውድቀት የነበየችው ነቢይት ዲቦራ በምድያም ሃያላት ያሸነፈችባቸው አምባ ነበረ። ስሙም ከዲቦራ አምባ ሊሆን ይችላል። በኋላም በነጌዴዎን ዘመን ያሕል በፈርዖኑ 2 ራመሠስ መዝገቦች ወደ ሶርያ ለዘመቻ ሲሄድ ሥራዊቱ «ደብረ ዳፑር» አምባን እንደ ከበበ ሲገልጽ፣ በአንዳንድ አስተሣሰብ ይሄ ማለት የደብረ ታቦር አምባ ሳይሆን አይቀርም።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |