አብርሃም

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

አብርሃምመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በዑር ከላውዴዎን አብራም ተወልዶ በኋላ ወደ ካራንና ወደ ከነዓን ግብፅም የሄደው የዕብራውያን፣ የእስማኤላውያንና የብዙ ሕዝቦች አባት ነበረ።

የአብርሃም ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ አብርሃም ሕይወት ብዙ ምዕራፍ ይሰጣል።

የአብርሃም ዕድሜ በመጽሐፈ ኩፋሌ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 • 1876 ዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ.) - አብራም ለአባቱ ታራ እና ለእናቱ ኤድና በዑር ከላውዴዎን ተወለደ።
 • 1886 ዓ.ዓ. - ሦራ (በኋላ ሣራ) ተወለደች (?)።
 • 1891 ዓ.ዓ. - አብራም ወጣት ሆኖ በከብት የሚስብ ማረሻ ፈጠረ።
 • 1903 ዓ.ዓ. - አብራም አባቱን ታራን በጣኦታት ለምን ታምናለህ ብሎ ጠየቀው።
 • 1925 ዓ.ዓ. - አብራም ሦራንን አገባት።
 • 1932 ዓ.ዓ. - ሎጥ ተወለደ።
 • 1936 ዓ.ዓ. - አብራም የዑርን አረመኔ መቅደስ አቃጠለና ወደ ካራን ሸሸ።
 • 1950 ዓ.ዓ. - የሰናዖር ንጉሥ አምራፌልና የኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምርሰዶምን አካባቢ በከነዓን ያዙ።
 • 1951 ዓ.ዓ. - እግዚአብሔር አብርሃምን ባረከው፣ አብርሃምም ሰማያዊ ቋንቋ ለመማር ጀመረ።
 • 1953 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከካራን ወደ ከነዓን ተጓዛ።
 • 1954 ዓ.ዓ. - ኬብሮን በከነዓን ተሠራ።
 • 1956 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ግብፅ ሄደ።
 • 1961 ዓ.ዓ. - ጣይናስ በግብጽ ተሠራ።
 • 1963 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ከነዓን ወደ ቤቴል ተመለሰ። ሰዶም በኤላም ላይ አመጸ።
 • 1964 ዓ.ዓ. - የነገስታት ጦርነት፦ የአብርሃም ሠራዊት አምራፌልን ወዘተ. አሸነፉ። አብርሃምም በምላሽ ስንኳ አንዳችም ሲባጎ ከሰዶም ንጉሥ እንዳይወስድ አሻፈረኝ ነገረለት።
 • 1965 ዓ.ዓ. - እስማኤል ተወለደ።
 • 1979 ዓ.ዓ. - እሳት ከሰማይ ወርዶ ሰዶምንና ገሞራን አጠፋ። አብርሃም ወደ ቤርሳቤ ሄደ፣ ይስሐቅ ተወለደ።
 • 1982 ዓ.ዓ. - እስማኤልና እናቱ ሀጋር ወደ ፋራን ምድረ በዳ ተሰደዱ።
 • 2003 ዓ.ዓ. - አብርሃምና ይስሐቅ ወደ ደብረ ጽዮን ተጓዙ፤ ወደ ቤርሳቤ ተመለሱ።
 • 2010 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከቤርሳቤ ወደ ኬብሮን ተመለሰ።
 • 2024 ዓ.ዓ. - ሣራ ዐረፈች፤ ለመቃበርዋም አብርሃም ዋሻ ከኬጢያውያን ሰው ከኤፍሮን ገዛ።
 • 2027 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ርብቃን አገባት፣ አብርሃምም ከጡራን አገባት።
 • 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብኤሳው ለይስሐቅ ተወለዱ።
 • 2060 ዓ.ዓ. - አብርሃም አረፈ።
: