ይስሐቅ
Appearance
ይስሐቅ (ዕብራይስጥ፦ יִצְחָק, /ዪጽሓቅ/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የአብርሃምና የሣራ ልጅ ነበረ። ርብቃን አግብቶ መንታ ልጆቻቸው ዔሳው እና ያዕቆብ በሌላ ስማቸው ኤዶምያስና እስራኤል የተባሉትን ሁለት ብሔሮች ወለዱ።
የይስሐቅ ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ይስሐቅ ሕይወት ብዙ ይጻፋል።
- 1979 ዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ.) - ሰዶምና ገሞራ ጠፍተው አብርሃምና ሣራ ከቤቴል (ሎዛ) ተነሥተው በቤርሳቤ ሠፈሩ፣ ይስሐቅ ተወለደ።
- 1982 ዓ.ዓ. - የይስሐቅ ታላቅ ወንድም እስማኤልና እናቱ አጋር ወደ ፋራን ምድረ በዳ ተሰደዱ።
- 2003 ዓ.ዓ. - አብርሃምና ይስሐቅ ወደ ደብረ ጽዮን ተጓዙ፤ ወደ ቤርሳቤ ተመለሱ።
- 2010 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከቤርሳቤ ወደ ኬብሮን ተመለሰ።
- 2027 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ከካራን የነበረችውን ርብቃን አገባት።
- 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብ (እስራኤል)ና ዔሳው (ኤዶምያስ) ለይስሐቅ ተወለዱ።
- 2060 ዓ.ዓ. - አብርሃም አረፈ።
- 2073 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ከኬብሮን ወደ ቤርሳቤ ተመለሰ።
- 2081 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ በጌራሮ ሠፍሮ ከፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቢሜሌክ ጋር ስምምነት ተዋዋለ።
- 2101 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ከጌራሮ ወጣ።
- 2108 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤ ተመለሰ።
- 2114 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ያዕቆብን ለዔሳው ስቶ ርስቱን ሰጠው።
- 2162 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ አረፈ።