Jump to content

ጌራራ

ከውክፔዲያ

ጌራራ (ዕብራይስጥ፦ גְּרָר /ግራር/) በኦሪት ዘፍጥረት የሚጠቀስ የፍልስጥኤማውያን ከተማ ነው። በቤርሳቤ አካባቢ ይገኝ ነበር።

መጀመርያው የሚጠቀሰው በምዕራፍ ፳ ሲሆን አብርሃም በጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ግዛት እየኖረ ሚስቱ ሣራ እኅቴ ነች በማለት አቢሚሌክን እንዳታለለ ይወራል። ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ታሪክ ስለ ሣራና የግብጽ ፈርዖን አለ።

ከዚያ በኋላ በምዕራፍ ፳፮ ይስሐቅ ደግሞ በአቢሜሌክ ግዛት ሲኖር ሚስቱ ርብቃ እኅቴ ነች በማለት እንዲህ ያደርጋል።

መጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት ግን፣ የአብርሃምና ሣራ ታሪክ ከፈርዖን ጋር፣ የይስሐቅና ርቅቃም ታሪክ ከአቢሜሌክ ጋር ብቻ ይሰጣል። የአብርሃምና ሣራ ታሪክ ከአቢሜሌክ ጋር በኩፋሌ ስለማይታይ፣ ከሌሎቹ ሁለት ታሪኮች በመቀላቀል እንደ ተሳተ የሚል ሀሣብ አለ። በዚህ መጽሐፍ የከተማው ስም «ጌራሮ» የንጉሡም ስም «አቤሜሌክ» ተጽፈዋል።