ሰዶም

ከውክፔዲያ
ሰዶም
סְדוֹם
የሰዶም ጥፋት፣ በ1844 ዓ.ም. እንደ ተሳለ
ሥፍራ
ሰዶም is located in ዮርዳኖስ
{{{alt}}}
ዘመን 2236-2092 ዓክልበ. ግድም
ዘመናዊ አገር ዮርዳኖስ
ጥንታዊ አገር ከነዓን

ሰዶምኦሪት ዘፍጥረት ዘንድ በከነዓን አገር በሲዲም ሸለቆ፥ በጨው ባሕርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ የነበረ ከተማ ነው።

ጸሓፊዎቹ ሚካኤል ሶርያዊው (12ኛው ክፍለ ዘመን) እና አቡል ፋራጅ ወይም ባር ሄብራዩስ (13ኛው ክፍለ ዘመን) እንደ ተረኩ፣ «አርሞኒስ» (አርሞንኤም) የተባለ ከነዓናዊ ሰው ሁለት ወንድ ልጆች ሰዶምና ዐሞራ (ገሞራ) ወልዶ በያንዳንዱ ስም አዲስ ከተማ መሠረተ፤ ከዚህ በላይ ሦስተኛ ከተማ በእናታቸው ስም ሳዓር (ዞዓር) ሠራ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ፣ በሲዲም ሸለቆ የተገኙት 5 ከተሞች ሰዶም፣ ገሞራ፣ አዳማሰቦይም እና «ዞዓር የተባለች ቤላ» ናቸው። ለ12 ዓመታት ለኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምር ከተገዙ በኋላ በ13ኛው ዓመት አመጹ፣ በ14ኛውም ዓመት ኮሎዶጎምር፣ የሰናዖር ንጉሥ አምራፌልና ጓደኞቻቸው የእላሳር ንጉሥ አርዮክና «የአሕዛብ ንጉሥ» ቲርጋል ሁላቸው ከተሞቹን እንዲመቱ ዘመቱ። የአብርሃም ዘመድ ሎጥ በዚህ ሠፈር ይኖር ስለ ነበር እሱም ተማረከ። ከዚህ በኋላ ግን አብርሃም ሰምቶ ከ318 ሎሌዎቹ ጋር ተነሥቶ እነኮሎዶጎምርን አሸነፋቸው፣ ሎጥንም ነጻ አደረገው። የሰዶም ንጉሥ ስም በዚያው ወቅት ባላ ተባለ።

የሲዲም ሸለቆ ኗሪዎች እጅግ ክፉዎች ነበሩ፣ እስካሁንም 'ሰዶማዊ' 'ሰዶማውያን' 'ሰዶማዊነት' 'ግብረ ሰዶም'፣ እና 'ገሞራው' የሚሉት ዘይቤዎች ስለ ጸባያቸው ይመሰክራሉ።

ከጦርነቱ ጥቂት ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር እንደ ሦስት ሰዎች ወይም መላዕክት በተዓምር ለአብርሃምና ለሚስቱ ሣራ ታየ። ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል ሰዶምን ሊያጥፋው እንደነበር ለአብርሃም ገለጸ። ከውይይታቸው በኋላ ቢያንስ 10 ጻድቃን ከተገኙበት በምሕረቱ እንዳያጠፋው ይስማማል። ከዚያ ከሰዎቹ (መላዕክቱ) 2ቱ ወደ ሰዶም ወደ ሎጥ ቤት ወጡ።

የሰዶም ጥፋት፣ 1510 ዓ.ም. ግድም እንደ ተሳለ

የሰዶም ኗሪዎች ማንኛውም የዋህ ሰው በሠፈራቸው እንዳያልፍበት ደስ አላላቸውም ተበሳጩም። እንደ አገራቸው ልማድ ከሎጥ ቤት ውጭ ተሰብስበው ሰዎቹን በግፍ እንዲይዙ ለማስገድ ሞከሩ። ሎጥ እምቢ ሲላቸው እንኳን የደጁን መዝጊያ ለመስበር ጣሩ። መላዕክቱ ግን ሰዶማውያንን አሳወሩዋቸው። ከዚያ ሎጥና ቤተሠቡ ሳይጠፋ ከሰዶም ቶሎ እንዲያመልጡ አዘዟቸው። ስለዚህ ሎጥና ቤተሠቡ ወደ ዞዓር ሸሹ። እግዚአብሔርም እሳትና ዲን በሰዶምና በገሞራ ላይ አዘነበ።