ቤቴል

ከውክፔዲያ
አብርሃም መሥዊያ የሠራበት ሥፍራ በዚሁ ግንብ ፍርስራሽ ቦታ እንደ ነበር ይታመናል።

ቤቴል (ዕብራይስጥ: בית אל /በይት ኤል/ «የአምላክ ቤት») ከመጽሐፍ ቅዱስ የታወቀ በጥንታዊ እስራኤል የተገኘ ከተማ ነበር። እስራኤላውያን ከከነዓን ከያዙት አስቀድሞ ሎዛ («ሉዝ») የተባለች ከተማ በዚያ ነበረች። አብርሃምይስሐቅያዕቆብ በከነዓን ሲቆዩ መኖርያቸውን ካደረጉባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። አሁን ሥፍራው በፍልስጤም ግዛቶች ሲሆን ቤቲን ከተባለች መንደር ዙሪያ ይገኛል።