Jump to content

የተሰሎንቄ ዐዋጅ

ከውክፔዲያ
ቴዎዶስዮስ

የተስሎንቄ ዐዋጅመጋቢት 1 ቀን 372 ዓም ከሮሜ መንግሥት ባለሥልጣናት በተሰሎንቄ ግሪክ አገር የወጣ ዐዋጅ ነበረ። በዚህ ዐዋጅ ቄሣሮቹ በተለይም ቄሳር ቴዎዶስዮስሥላሴ ማመን የመንግሥት ሃይማኖት አደረገ።

305 ዓም ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ከምሥራቁ ቄሣር ሊኪኒዩስ ጋራ የሚላኖ ዐዋጅ አውጥተው ነበር። ያው ዐዋጅ ለክርስቲያኖች መታገሥና ከመከራዎች ነጻነት ያረጋገጠ ነው። በ318 ዓም ግን የአሪዩስ ትምህርት ወይም አሪያኒስም ተስፋፍቶ ነበር፤ አሪዩስም እንዳስተማረ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ወልድ ከእግዚአብሔር አብ በታች የተለየና የተፈጠረ አምላክ እንደ ነበር አለ፣ እንጂ ሥላሴን አላስተማረም። ስለዚህ በዚያው ዓመት ክርክሩን ለመፍታት የንቅያ ጉባኤ ተጠራ። ጉባኤው የአሪያኒስም ክርክር ትቶ ኢየሱስ «ዕውነተኛ አምላክ»ና «ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ አለው» በማለት የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትን አዘጋጁ።

ነገር ግን የአሪያኒስም ክርክር በዚህ ጉባኤ ጸት አላለም ነበር። የአሪዩስ ወገን ይበረታ ነበር፤ ከቆስጠንጢኖስም የተከተለው ንጉሥ ልጁ 2 ቆስጠንቲዩስ ዝንባሌ ለአሪያኖች ነበር። ከእርሱም የተከተለው ዩሊአኖስ ከሐዲ የድሮ አረመኔነት ወዳጅ ነበርና የንቅያ ክርስትናን ለማቃወም ማናቸውንም ዓይነት ሌሎችን እምነቶች ይደግፍ ነበር። ከሦስት ዓመታት ብቻ በኋላ ግን ዩሊያኖስ በፋርስ ጦርነት ዓረፈና አዲሱ ንጉሥ ዮቪያኑስ እንደገና ክርስቲያን ነበር።

እስከ 371 ዓም ድረስ ከጤዎዶስዮስ በፊት በምሥራቅ የነገሠው ቫሌንስ የአሪያኒስም ምእመን ሆኖ ነበር። በምዕራቡ መንግሥት ግን የሕዝቡ ዋናው እምነት የንቅያ (የሥላሴ) እምነት ነበር። ቴዎዶስዮስ እራሱ በእስፓንያ ተወልዶ የንቅያ ምዕመን ሲሆን በዚያን ጊዜ እሱ የምሥራቅ መንግሥት ቄሣር ሆነ። የምዕራብ ቄሣሮች ግራቲያንና የ፭ ዓመት ልጅ 2 ዋሌንቲኒያን ሲሆኑ ግራቲያን ደግሞ የንቅያ እምነት ደጋፊ ነበር። ስለዚህ ሦስቱ ቄሣሮች በተሰሎንቄ ተገኛኝተው በተሰሎንቄ አዋጅ ተስማሙ።

IMPPP. GR(ATI)IANUS, VAL(ENTINI)ANUS ET THE(O)D(OSIUS) AAA. EDICTUM AD POPULUM VRB(IS) CONSTANTINOP(OLITANAE).
Cunctos populos, quos clementiae nostrae regit temperamentum, in tali volumus religione versari, quam divinum Petrum apostolum tradidisse Romanis religio usque ad nunc ab ipso insinuata declarat quamque pontificem Damasum sequi claret et Petrum Aleksandriae episcopum virum apostolicae sanctitatis, hoc est, ut secundum apostolicam disciplinam evangelicamque doctrinam patris et filii et spiritus sancti unam deitatem sub pari maiestate et sub pia trinitate credamus. Hanc legem sequentes Christianorum catholicorum nomen iubemus amplecti, reliquos vero dementes vesanosque iudicantes haeretici dogmatis infamiam sustinere ‘nec conciliabula eorum ecclesiarum nomen accipere’, divina primum vindicta, post etiam motus nostri, quem ex caelesti arbitro sumpserimus, ultione plectendos.
DAT. III Kal. Mar. THESSAL(ONICAE) GR(ATI)ANO A. V ET THEOD(OSIO) A. I CONSS.
ነገሥታት ግራቲያን፣ ዋሌንቲኒያንና ጤዎዶስዮስ ቄሳሮች (አውግስጦሶች)። ዐዋጅ ለቁስጥንጥንያ ሕዝብ።
በምኅረታችንና በትዕግስታችን የተገዙት መላ ሕዝብ ይህን እምነት እንዲከተሉ እንመኛለን፤ ያውም በቅዱስ ሐዋርያው ጴጥሮስ ለሮማውያን የወረደው እምነት፣ ከእርሱም እስካሁን የተናገረው እና ፓፓ ዳማሱስ እና የእስክንድርያ ጳጳስ ጴጥሮስ፣ የቅዱስ ሀዋርያዊ ሰው፣ የሚከተሉት ነው፤ ይህም፣ በሀዋርያዊ ጥናትና በወንጌል ትምህርት መሠረት፣ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ አሀድ አምላክ፣ በእኩል ክብርና በቅዱስ ሥላሴ እናመን። ይህን ሕግ ለሚከተሉት የካቶሊክ ክርስቲያኖች ስም ፈቃድ እንሰጣለን፣ ሌሎች ግን ጠማማዎችና እብዶች ተቆጥረው የሀረ ጤቃ መጥፎ ስም እንዲሰጡ እናዝዛለን፣ 'ወይም ስብሰቦቻቸው የቤተ ክርስቲያኖች ስም አይቀበሉም'፣ በመጀመርያ የአምላክ መዓት፣ በኋላም ከሰማይ ፍርድ የምንቈርጠው ቅጣታችን እንዳይደርስባቸው።
ተሰጠ ፫ ማርች በተሰሎንቄ በግራቲያኑስ አውግስጦስ ፭ኛ እና በቴዎዶስዮስ አውግስጦስ ፩ኛ ቆንስላነቶች።

በዚህ ወቅት ከሮሜ መንግሥት ውጭ ከሆኑት ክርስቲያን ብሔሮች መካከል፣ በአክሱም መንግሥት፣ በአርሜኒያ፣ በካውካሶስ ኢቤሪያና በካውካሶስ አልባኒያ የተገኙት ክርስቲያኖች የንቅያ (የሥላሴ) ደጋፊዎች ነበሩ። ጎታውያንጌፒዶችቫንዳሎች የተባሉት ጀርመናዊ ብሔሮች ግን የአሪያን ቤተክርስቲያን ምዕመናን ነበሩ።