መጋቢት ፩
Appearance
(ከመጋቢት 1 የተዛወረ)
መጋቢት ፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፹፩ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፷፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፹፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፹፬ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፺፱ ዓ/ም - በጎጃም ምድር ጎል በተባለ ሥፍራ የንጉሥ አጼ ያዕቆብ እና የአጼ ሱስንዮስ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው ድሉ የሱስንዮስ ሆነ። አጼ ያዕቆብ እና ጳጳሱ ዳግማዊ ጴጥሮስ በዚሁ ጦርነት ላይ ሞቱ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ዮሐንስ ራብዐዊ በትልቅ ጦርነት መተማ ላይ ከደርቡሾች ጋር ሲዋጉ በእነሱ እጅ ወደቁ። ሱዳኖቹ አንገታቸውን ቆርጠው እንጨት ላይ ሰክተው ገበያ ለገበያ ለሕዝባቸው አሳዩት።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - አዲስ አበባ፣ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ባካሄዱት አመጽ ትምህርት ቤቱ ለጊዜው ተዘግቶ ዋለ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ከኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበራት ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቁ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአልቃይዳ መሥራችና መሪ ኦሳማ ቢን ላደን።
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660-ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 -ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |