Jump to content

የውሃ ኡደት

ከውክፔዲያ
የ22:16, 5 ኖቬምበር 2021 ዕትም (ከ93.157.169.14 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የውሃ ኡደት ሥዕላዊ መግለጫ
በናሳ የተሰራ ቪድዮ (እንግሊዝኛ)

ውሃ ኡደት ማለት በሰማይ፣ በምድር ላይ እና ከምድር በታች ያለው የማያቋርጥ የውሃ እንቅስቃሴ ማለት ነው። ውሃ እየተነነ፣ እየጤዘ፣ እየዘነበ፣ እና ከምድር ውስጥ እየሰረገ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላው ይዘዋወራል። በሚዘዋወርበትም ጊዜ ከፈሳሽነት ወደ በረዶ እና ጋዝ ይለዋወጣል። በዚህም መልክ ውሃ ሲዘዋወር ውሃው ይጣራል፣ ጨው አልባ ይሆናል፣ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችንም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያመላልሳል። በተጨማሪም ድንጋይን በመሸርሸር እና አፈርና አሸዋ በማዝቀጥ የዓለምን መልክዓ ምድር ይለውጣል።

የውሃ ኡደት ኃይል /energy/ መለዋወጥን ያካትታል። ይህም የሙቀት ልክ ከፍና ዝቅ እንዲል ያደርጋል። ለምሳሌ፦ ውሃ ሲተን ኃይል ስለሚወስድ አካባቢውን ያበርዳል።