አቢሳሬ
Appearance
አቢሳሬ ከ1817 እስከ 1806 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ ፪ኛ ንጉሥ ነበረ። የጉንጉኑም ተከታይ ነበር። የአቢሳሬ አባት ስም አይታወቅም።
ኡር ደግሞ በግዛቱ ውስጥ ነበረችና በአንዳንድ ጽሑፍ አቢሳሬ «የኡር ንጉሥ»፣ «የኡርና የላርሳ ንጉሥ» ወይም «የአሞራውያን አለቃ» በሚሉት ማዕረጎች ይጠራል። ኒፑር ግን ወደ ላርሳ ተወዳዳሪ ወደ ኢሲን ንጉሥ ኡር-ኒኑርታ ስለ ተመለሠ፤ አቢሳሬ «የሱመርና የአካድ ንጉሥ» የሚለውን ማዕረግ አልደፈረም።
ለዘመኑ ከ፲፩ የዓመት ስሞቹ ሁላቸው በሙሉ ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦
- 1817 ዓክልበ. ግ. - «አቢሳሬ ንጉሥ የሆነበት ዓመት»
- 1809 ዓክልበ. ግ. - «አቢሳሬ በመሣርያዎቹ የኢሲንን ሥራዊት የመታበት ዓመት»
የአቢሳሬ ተከታይ ሱሙኤል ነበረ፤ የሱሙኤልም አባት ስም አይታወቅም።
ቀዳሚው ጉንጉኑም |
የላርሳ ንጉሥ 1817-1806 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሱሙኤል |
- የአቢሳሬ ዓመት ስሞች
- የላርሳ ንገሥታት Archived ኦክቶበር 21, 2012 at the Wayback Machine (እንግሊዝኛ)