Jump to content

እስኩቴስ

ከውክፔዲያ
የ22:29, 4 ሜይ 2023 ዕትም (ከPersian Lad (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
በካርታው አረንጓዴ አካባቢ እስኩቴሶች እና ሌሎች የኢራናውያን ህዝቦች

እስኩቴስ (ግሪክ፦ Σκυθία /ስኩጢያ/) በአውሮጳና በእስያ የተገኘ ጥንታዊ አገር ነበረ።

የእስኩቴስ ሰዎች (ግሪክ፦ Σκύθες /ስኩጠስ/) በታሪክ መዝገቦች መጀመርያ የሚታዩ በ700ዎቹ ዓክልበ. ሲሆን በአሦር ሰነዶች ውስጥ አሽኩዝ ተብለው ነው። ዳሩ ግን በኋላ ዘመን በጻፉት መምህሮች አፈ ታሪክ ዘንድ ከማየ አይኅ ቀጥሎ ከሁሉ አስቀድሞ የኖረ አገር ነበሩ። በቋንቋቸው በእስኩቴስኛ ለራሳቸው የነበራቸው ስያሜ ስኩዳ እንደ ነበር ይመስላል። በምሥራቅ አገሮች ግን ሳካዎች (ፋርስኛሳካቻይንኛ፦ 塞 /ሳይ/) ተባሉ። ግዛታቸው እጅግ ሰፊ ሆኖ ለረጅም ዘመን ከዳኑብ ወንዝ በአውሮጳ እስከ ሞንጎልያቻይናሕንድ ጠረፍ ድረስ ይስፋፋ ነበር።

በአውሮጳም ሆነ በእስያ ከአይርላንድ እስከ ካምቦድያ ድረስ በጣም ብዙ ብሔሮች ከእስኩቴሳውያን እንደተወለዱ የሚል ልማድ አላቸው።