Jump to content

Danger Man

ከውክፔዲያ

Danger Man (አደጋ ሰው) ከ1960 እስከ 1968 እ.ኤ.አ. ድረስ በኢንግላንድ የተሠራ የሰላይ ድራማ ነው።

«የአደጋ ሰው» ጆን ድሬክ ሲሆን ቅዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የናቶ ሰላይ ናቸው። መቸም ኹኔታው አደገኛ ሲሆን የሚጠሩት እሱ ነው። በዚሁም ሚና በአለም ዙሪያ ይጓዛል።

ከ1960 እስከ 1962 እ.ኤ.አ. ድረስ 39 የ 30 ደቂቃ ክፍሎች ተሠሩ። ከዓመት ፋታ በኋላ፣ ከ1964-1966 እ.ኤ.አ. 45 የአንድ ሰዓት ክፍሎች ተጨመሩ፤ እነዚህም አለም አቀፍ (ኢትዮጵያም) የተሠራጩት ነበሩ። በመጨረሻም በ1968 እ.ኤ.አ. 2 ተጨማሪ ክፍሎች ተደረጉ፣ ሁለቱም አንድላይ ደግሞ እንደ 2-ሰዓት ፊልሙ «ኮሮሺ» ታይተዋል።