Dr Kildare

ከውክፔዲያ
ዶ/ር ክልዴር

Doctor Kildare (ዶ/ር ክልዴር) ከ 1961 እስከ 1966 እ.ኤ.አ. ድረስ የተሠራ አሜሪካዊ ቴሌቪዝን ድራማ ስለ ሕክምና ነው። ሐኪሙ ዶ/ር ክልዴር በአንዱ የኑ ዮርክ ከተማ ሆስፒታል ውስጥ የሕዝቡን ጤና በመጠብቅ፣ ስኬታማና ለኅብረተሠብ አሳቢ የሆነ አራያ ነው። ስለዚህም በጣም የተወደደ ታሪክ ሆነ።

በመጀመርያ አራት አመቶቹ ላይ፣ 133 ክፍሎች እያንዳንዱም አንድ ሰዓት ተሠርተዋል። ለመጨረሻው አመት 58 የ 30 ደቂቃ ክፍሎች ተጨመሩ።