Gunsmoke

ከውክፔዲያ
ማርሻል ማት ዲሎን የሕግ ባለሥልጣን

Gunsmoke (የጠመንጃ ጢስ) ከ1955 እስከ 1975 እ.ኤ.አ. የተሠራ አሜሪካዊ ድራማ ትርዒት ነበረ። በአሜሪካ አገር ምዕራብ፣ በዶጅ ሲቲካንዛስ 1877 እ.ኤ.አ. አካባቢ፣ ብዙ ወንጀለኞች በሚደርሱበት ከተማ ሲሆን የቦታው ዋና ባለሥልጣን ፣ ማርሻል ማት ዲሎን ሕጉን ለመመሥረት ሀላፊነት ያለው ነው። ለሀያ አመት በመቆየቱ በአሜሪካ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ እጅግ የተወደደ ፕሮግራም ሆኖ ይታወሳል።

233 የ30 ደቂቃ ክፍሎች ከተሠሩ በኋላ፣ 402 የአንድ ሰዓት ክፍሎች ተጨመሩ።