Here's Lucy
Appearance
Here's Lucy («ሉሲ እዚህ አለች») ከ1968 እስከ 1974 እ.ኤ.አ. ድረስ የተሠራ አሜሪካዊ ቴሌቪዥን ተርዒት ነበር። ለዝነኛዋ ተዋናይት ሉሲል ባል ሦስተኛዋ አስቂኝ ተከታታይ ነበር፤ ይሄም ከI Love Lucy («ሉሲን እወዳታለሁ»፣ 1951-57 እ.ኤ.አ.) እና The Lucy Show («ዘ ሉሲ ሾው» 1962-68 እ.ኤ.አ.) ቀጥሎ ነበር።
በዚሁ ተከታታይ ትርዒት ውስጥ፣ ብሌን ለብሌን የምትይዝ ስመ ጥሩዋ ክቡር የሉሲል ባል ሚና «ሉሲ ካርተር» ሆኖ ለ«ትንግርት ሥራ ማስገኛ ድርጅት» ሎስ አንጄሌስ ለአጎትዋ እየሠራች ብዙ ቧልት እና የዘመኑን ቄንጥ ያቀርባል። በውጭ አገርም በሰፊ ተሠራጭቶ ነበር።