Jason King

ከውክፔዲያ
ተወናዩ ፒተር ውንጋርድ የ70ዎች ቄንጥ አራያ

Jason King (ጄሰን ኪንግ) ከ1971 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ድረስ የተሠራ የእንግሊዝ አገር ቴሌቪዝን ፕሮግራም ነበር። ከቀደመው ተመሳሳይ ፕሮግራም Department S (1969-70 እ.እ.አ.) የተከታተለ ነበር።

በትርዒቱ ውስጥ ጄሰን ኪንግ (ፒተር ውንጋርድ) በሎንዶን የሚኖር ልብ ወለድ ደራሲ ነው። የሚጽፈውም ልብ ወለድ ስለ ወንጀል መርማሪ ዠብዱዎች ነው። ቢባልም ሰውየው ጄሰን ኪንግ የራሱን ዠብዱዎች መቸም አያጣም። በተለይ የሚያዝናናው የዘመኑ ደማቅ ዝንጠኛነት ሲሆን በኢትዮጵያም ተቀባይነት ካገኙት ባዕድ ፕሮግራሞች መኃል ተቆጥሯል።