Riuadusualihin(ሪያዱሷሊሂን)

ከውክፔዲያ

ሪያዱሷሊሂን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ቅንነትና ታማኝነት
  • ሁለት
  • ሦሥት
    • ቅንነትና ታማኝነት**

(ኢኸላስ) እንዲሁም ተነሳሽነት (ኒያህ በማንኛውም ንግግርና ተግባር ግልፅ ይሁን ድብቅ አላህ እንዲህ ብሉያል አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡ ( አልብይዮነህ) 5 አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ (አልሀጅ 37) በደረቶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ብትደብቁ ወይም ብትገልፁት አላህ ያውቀዋል፡፡ ( አል ኢምራን 29) 1, ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ,ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶ,ዐ,ወ)እንዲህ ብለዋል ስራ የሚለካው በሀሳብ (በኒይያህ ) ነው። ማንኛውምንም ሰው ያሰበውን ያገኛል ። ስደቱ ወደ አላህና መልክተኛው የሆነ ስደቱ ወደ አላህና መልክተኛው ነው የስደቱ ግብ አለማዊ ጥቅም (ዱንያ) ወይም አንዲት ሴትን ሊያገባት ከሆነ፣ ስደቱ ለተሰደደበት አላማ ነው ። ( ቡኻሪና ሙስሊም) ከሀዲሱ የምንማራቸው ቁምነገሮች አንድ ተግባር ከመከናወኑ በፊት መልካም ተነሳሽነት (ኒይያህ) አስፈላጊ እንደሆነ ዑለሞች ተስማምተውበታል ። የዚያን ተግባር ምንዳ ማግኘት ይቻል ዘንድ ። ግና ማንኛውንም ተግባር ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ የግድ ኒይያህ ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም? በሚለው ነጥብ ላይ ተወዛግበዋል የሻፊዒይ መዝሀብ ምሁራን እንደ ውዱእ ባሉ የዒባዳ ዝግጅቶችም ሆነ እንደ ሰላት ባሉ አከባዳወች ላይ ኒይያህ እንደ(ቅድመ መስፈርት) ነው ሲሉ የሀነፊይ መዝሀብ ምሁራን ደግሞ በዒባዳወች ላይ እንጂ ለዒባዳ በሚደረጉ ዝግጁቶች ላይ ኒይያህ እንደማያስፈልግ ይናገራሉ። _ የኒይያ ማእከል ቀልብ (ልቦና)ነው። አንድን ተግባር ለማከናወን በልቦና ማሰቡ ብቻ በቂ ነው።መናገሩ አያስፈልግም ። ተግባርን ለአላህ ብቻ በ"ኢኽላስ" በቅንነት ማከናወንን ለተቀባይነቱ ዋስትና ይሰጣል።አላህ በርሱ ብቻ በቅንነትና በታማኝነት (ኢኽላስ) የተከናወነን ተግባር አንጅ አይቀበልም። 2።የሙእሚኖች እናት አኢሻ (ረአ)እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል የአላህ መልከተኛ ሶ,አ,ወ ካእባን ከማውደም የሚተም አንድ ሰራዊት ይዘምታል ከአንድ ምድረ በዳ መሬት ላይ ሲደርስ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሉት ሁሉም በመሬብት መሰንጠቅ ይዋጣሉ በማለት ተናገሩ እንዴት ከመጀመሪያው እሰወከመጨረሻው ያሉት ሁሉም በመሬት መሰንጠቅ ይዋጣሉ በማለት ተናገሩ። እንዴት በመሬት መሰንጠቅ እንዲዋጡ ይደረጋል ? በመካከላቸው የንግድ ሰወችና ሌሎችም (አላማቸው ከእባ ማፍረስ ያልሆኑ ሰወች እያሉ? አልኳቸው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው (በሁሉም) ይዋጣሉ ከዚያም እንደየኒያቸው ይቀሰቀሳሉ በማለት ገናገሩ ( ቡኻሪ ሙስሊም የሀዲሱም ቃል የቡኻሪ ነው) 3, ዓኢሻ (ረ,ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ ሶ,ዐ,ወ እንዲህ ብለዋል ከመካ (በድል) መከፈት ቡሀላ ስደት የለም ።ግና ጂሀድና ፣ኒይያህ ምንግዜም ይኖራሉ ። (ለጂሀድ) እንድትዘምቱ በምትጠየቁበት ጊዜ ዝመቱ።(ቡኻሪና ሙስሊም). ከሀዲሱ የምንማራቸው ቁምነገሮች አንዲት ሀገር ኢስላማዊ (ዳረል ኢስላም) ከሆነች ቡሀላ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ አይፈቀድም አንዲት አገር የኩፍር ሀገር ( ዳረል ኩፍር) እስከሆነችና ሙስሊሞች በዚያች ሀገር ላይ ኢስላምን ተግባራዊ ለማድረግ እስከተሳናቸው ድረስ ስደት ግዴታ እንደሆነ ይቆያል ወደ ጂሀድ ጥሪ በሚመጣበት ወቅት አፋጣኘ ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ ሁሌም ጂሀድን ማሰብና ለጂሀድ ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ተገቢ ነው

    • ሁለት**

4ኛ አቢ አብደላህ ኢብኑ ጃቢር ዐብደላሀደ አል አንሷሪይ (ረ,ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል በአንድ ዘመቻ ላይ ከነብዮ (ሶ,ዐ,ወ )ጋር ነበርን ። እንዲህ አሉ መዲና ውስጥ በሽታ (ከዘመቻ) ያስቀራቸው ሰወች አሉ ።መንገድን አልሄዳችሁም ፣ሸለቆንም አላቋረጣችሁም ከናንተ ጋር ቢሆን እንጂ በሌላ ዘገባ ደግሞ፡-"በምንዳ የተጋሯችሁ ቢሆን እንጂ" የሚል ተመልክቷል፡፡(ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)ቡኻሪ አነስን ጠቅሰው እንደዘገቡት፡-"ከተቡክ ዘመቻ ተመለስን፡፡ ከነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር፡፡"ከኋላችን መዲና ውስጥ ችግር (ዑዝር) ከዘመቻያስቀራቸው ሰዎች አሉ፡፡ ጋራ ሸንተረሩን አላቆራረጥንም፥ከኛ ጋር የሆኑ ቢሆን እንጂ" በማለት ተናገሩ፡፡ (ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር- በአንዳች) አስገዳጅ ምክኒያት ከጅሃድ የቀረ ሰውመልካም ኒይያና ፍላጎት እስካለው ድረስ ጅሃድ ያደረጉሰዎችን ምንዳ ያገኛል፡፡


5. አቡ የዚድ መዕን ኢብኑ የዚድ ኢብኑ አል-አኽነስ(ረ.ዐ) -እርሳቸውም፥ አባታቸውም፥ አያታቸውምሶሐባዎች ነበሩ- እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-አባቴ የዚድ ለምፅዋት የተወሰኑ ዲናሮችን አወጣናመስጊድ ውስጥ ለአንድ ሰው መፀወተ። መጣሁናአነሳኋቸው፥ ወደርሱም ይዣቸው መጣሁ፡፡ "በአሏህእምላለሁ! ለአንተ አላሰብኳቸውም ነበር" አለ፡፡መልእክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) ዘንድ ሞገትኩ፡፡ "የዚድ ሆይ!ለአንተ ያሰብከው አለህ፥ (የኒይያህን ዋጋ ታገኛለህ፡፡)መዕን ሆይ! ለአንተ ደግሞ የያዝከው አለህ" አሉ፡፡(ቡኻሪና ሙስሊም)ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች- ሱንና የሆነን ምፅዋት ለልጆች መስጠት ይፈቀዳል፡፡ዘካን ግን ለልጆችም ሆነ ለወላጆች መስጠትአይፈቀድም፡፡- ሶደቃን በወኪል ማሰራጨት ይፈቀዳል፡፡ 6. ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (ረ.ዐ) - ጀነትከተመሰከረላቸው አስር ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው-እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡- የመሰናበቻ ሐጅ ዓመትወቅት ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሊጠይቁኝ መጡ፡፡ ብርቱ በሽታአሞኝ ነበር፡፡ "በኔ ላይ የምታዩት በሽታ ደርሶብኛል፡፡በርካታ ንብረት አለኝ፡፡ ከአንዲት ሴት ልጅ ሌላ ወራሽየለኝም። የገንዘቤን ሁለት ሶስተኛ ልመፅውትን?"አልኳቸው። "አይሆንም" አሉኝ፡፡ "የአሏህ መልዕክተኛሆይ! ግማሹንስ?" አልኳቸው፡፡ "አይሆንም" አሉኝ፡፡"የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ሲሶውንስ?" አልኳቸው፡፡"ሲሶ" ሲሶም ብዙ -ወይም ትልቅ- ነው፡፡ ወራሾችህን ሀብታሞች አድርገህ ማለፍህ ድሀዎችና የሰዎችን እጅየሚያዮ አአድርገሀቸው ከሞትህ የበለጠ ነው። የአላህውዴታ በመሻት አንድንም ምፀዋት አትማፀኑም ምንዳያገኝህበት ቢሆን እንጂ። በባሌ ቤትህ አፍበምታስቀምጠው (ጉርሻ) እንኳን ቢሆን ምንዳ ታገኛለህአሉ። ከባልደረቦቼ ተነጥዬ ወደኋላ እቀራለሁኝ አልኳቸውወደ ኃላ ተነጥለህ ቀርተህ የአላህ ውዴታ በመሻትመልካምን ተግባር አትፈፅምም።ደረጃና ልእልናንየጨመርክ ቢሆን እንጂ።ምናልባትም ከፊል ሰዎችእንዲጠቀሙበት ጠላቶች ደግሞ በአንተ (ሰበብ)እንዲጎዱ ወደ ኋላ ትቀር ይሆናል።አላህ ሆይ የባልደረቦቼን ስደት አፅድቅ ወደኃላ አትመልሰቸው አሉ።ነገርግን የሚያሳዝነው ሰአድ ኢብን ኸወይላህ ነው።ኘካውስጥነበር የሞተው ነብዮ (ሰ አ ወ) ዐ ጅግ ያዝኑለትና በሞትየመለየት ነገር ይሰማቸው ነነር።ቡኻሪ ሙስሊም) ።# ከሀዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮችለመልካም አላማና ተግባር በሽታን ለሌሎች መናገርክልክልነት የለውም ለምሳሌ ፈውስ ወይም ዱአ በመሻት።ገንዘብን ሀላል በሆነ መንገድ መሰብሰብ ይፈቀዳልባለሀብቱ ሀላፊነቱ ጠብቆ እስከተወጣ ድረስ ሃብትማከማቸቱ ከጥፋት ሊቆጠር አየገባም ።አንድ ሰው ወራሽ እስካልፈቀደለት ድረስ ከገንዘቡ ከአንድሶስተኛ በላይ ኑዘዜ ማድረግ አይፈቀድለትም።ሰዎች በመልካም ኒይያን እና ተነሳሽነት ለሚፈፅሙትተግባር ሁለ ምንዳ ያኛሉ።የቤተሰብን ቁሳዊ ፍላጎት ማሟላትም መልካምን ኒይያከታከለበት ምንዳ ያስገኛል 7 •አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ አወ) እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል አላህ ውጫዊ ቅርፅናውበታችሁ አይመለከትም ልቦናችሁ ነው የሚመለከተው።(ሙስሊም ዘግበውታል ። # ከሀዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮችበስራ መጠቀምና አጅር ማግኝት የሚቻለው ተግባሩከመልካም ኒያዎች ጋር የተቆራኘ እንዲሆን ብቻ ነው።ልቦናን የአላህ ቁጣ ሊያስከትሉ ከሚችሉ በሽታዎች ሁሉለማፅዳት ጥረት ማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠውየሚገባ ነው።ልቦናን የማፅዳቱ ተግባር ከሌሎች ተግባራት ይልቅቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ።ምክንያቱምለማንኛውም ስራ ና እንቅስቃሴ ተቀባይነት ማግኝትወይም ውድቀት መሆን ወሳኙ የቀልብ በአዳነት ወይምመበከልነውና።

    • ሦሥት**

8 አቡ ሙሳ ሙሳ ዐብደላህ ኢብኑ ቀይስ አል አሻሪይ ( ረ.ዐ) እንዳስተላለፊት :-የአላህ የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ለጀግንነት ስለሚዋጋ ለዘር ክብር ስለሚዋጋ ለይዩልኝ (ለዝናና ክብር ሲል ስለሚዋጋ ሰው የትኛውም በአላህ ጎዳና ላይ እንደሆኑ ተጠየቁ:: "የአላህ ቃል:-ቃል የበላይ ትሆን ዘንድ የሚፋለም፤በአላህ ጎዳና ያለ እርሱ ነው" ሲሉ ተናገሩ:: ቡኻሪና ሙስሊም ከሐዲሱ የምንማረው ቁም ነገር አንድ ተግባር ከአላህ ዘንድ ሊያገኝ የሚችለው በጥሩ ኒይያህ ከተፈፀመ ብቻ ነው:: በአላህ መንገድ ላይ የአላህን ቃል የበላይ ለማስጠበቅ ሲፋለሙ ሰማእት የሆኑ ብቻ ናቸው በቁርአንና በሀዲስ የተጠቀሱ የሰማዕታት እጣዎች ሊጎናፀፉ የሚችሉት ግና ከፍልምያው መስክ ላይ የወደቀ ሁሉ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::አይታጠብም ከፈንም አይለብስም ልብሱ ይቀበራል የ"ኒይያህ"ጉዳይ ለአላህ የተተወ ነው:: 9 አቡ በክረት ኑፈይስ ኢብኑ አል-ሀሪስ ከሥ ሱቀፊይ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል:- ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)"ሁለት ሙስሊሞች ሾተል ከተማዘዙ፥ገዳይም ሟችም፥እሳት ውስጥ ናቸው"በማለት ተናገሩ:"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ:ገዳይስ ይሁን የሟች ጥፋት ምን ሆኖ ነው:ለቅጣት የበቃው?::ስል ጠየቅኩ:: ወዳጁን ለመግደል ቋምጦ ነበር ሲሉ መለሱ:: ቡኻሪ ሙስሊም (ከሀዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮች) ወንጀል ለመፈፀም የአላህን ህግጋት ለመተላለፍ የቆረጠና ለውጊያ የሚያበቁ ቅድመሁኔታዎችን ሁሉ ያሟላ ወንጀሉን ፈፀመም አልፈፀመም ከተጠያቂነት አያመልጥም:: 10. አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-"አንድ ሰው በጀመአ በህብረት የሚሰግዳት ሶላት ከስራ ቦታው ወይም ከቤተሰቡ ከሚሰግድባት ሶላት ከሀያ ሶስት እስከ ሰላሳ ብልጫ አላት ይህም የሚሆነው በተሟላ መልኩ ውዱዕ ከፈፀመና ከዚያም ሰላትን እንጂ ሌላን ባለመሻት ከቤቱ የወጣበት አላማ ሶላት ብቻ ሆኖ ወደ መስጊድ ከመጣ ነው: ወደ መስጊድ ከመጣ ነው:: ወደ መስጊድ በሚያደርገው ጉዞ በእያንዳንዱ እርምጃ አንድ ደረጃ ከፍ ይደረግለታል::በዚያችው እርምጃ አንድ ኅጥያት ይታበስለታል መስጊድ እስኪገባ ድረስ መስጊድ ከገባ በኋላ መስጊድ ውስጥ ለመቆየቱ ምክንያት ሶላት ብቻ እስከሆነች ድረስ ሶላት ውስጥ እንዳለ ይቆጠርለታል ከእናንተ አንዳቹ የሰገደበትን ቦታ እስካለቀቀ ሰዋችን እስካላወከና ውዱእ እስካልፈታ መላይኮች አላህ ሆይ ምህረትን ለግሰው አላህ ሆይ ጸጸቱን ተቀበለው እያሉ ዱዓ ያደርጉለታል (ቡሀሪና ሙስሊም የሀዲሱ ቃል የሙስሊም ነው) (ከሀዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮች) - በስራ ቦታ ላይ ሶላት መስገድ ይፈቀዳል ምንም እንኳ ቅልብን ሰብስቦ ለመስገድ ስለማያስችል የሚጠላ ቢሆንም - መስጊድ ውስጥ በጀመዓ (በህብረት) የሚሰገድ ሶላት ለብቻ ከሚሰገደው ሶላት በ25፣26 ወይም27 ደረጃዎች