Shincheonji

ከውክፔዲያ

Shincheonji - የኮሪያዎች መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በኢትዮጵያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የምንከተለውና የዳንንበት ወንጌል በዘመናት መካከል ተግዳሮት ጠፍቶትና ከትግል ውጪ ሆኖ የሚያውቅበት ታሪክ የለም። በየወቅቱ ከውስጥና ከውጪ በሚነሱ የስህተት ትምህርቶችና ተቃውሞዎች ሳቢያ በየዘመናቱ ራሱን ሲከላከልና በተነሱበት ተቃውሞዎች ሁሉ እያሸነፈ ያለንበት ዘመን ላይ ደርሷል። አሁንም በተለይም ከተሀድሶ ዘመን በኋላ ለመቁጠር በሚታክቱ አያሌ የውጭና የውስጥ ተግዳሮቶች መካከል እያለፈ ሲሆን በተለይ ከውስጥ በሚነሱና ሰይጣን አስርጎ ባስገባቸው የወንጌሉ ጠላቶች ሳቢያ ቤተ ክርስቲያን ስትታመስ ኖራለች። በእኛም ዘመን በተለይ ከብልጽግና ወንዴል ጋር ተያይዞ አሌ የማይባሉ የምንፍቅና ትምርቶች የገቡ ሲሆን ከዚህ ቀጥሎ የምናየው የ Shincheonji ትምህርት ደግሞ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ለየት ብሎ ብዙም ትኩረት ሳይፈልግ በቀላሉ ሊታያ በሚችልበት ሁኔታ ትምህርቱን እያስፋፉ ይገኛል።

በርግጥ ይህ አስተምህሮ በጣም ግልጽ የሆነ ከወንጌሉ ያፈነገጠ ትምህርት ቢሆንም እንኳ በጣን በሆነ ሁኔታ የምንፍቅና ሥራውን እያቀላጠፈ ያለና እየተጠቀሙበት ካለው አካሄድ የተነሳም (Technical Strategy) ሰዎቻችን በተለይም አዳጊ ወጣቶች እና ወጣቶችን በከፍተኛ ቁጥርና ፍጥነት በመማረክ ላይ ይገኛል።

ወደ አስተምህሮው እንግባ

Shincheonji በደቡክ ኮሪያ የተነሳ የስህተት ትምህርት ሲሆን አስተማሪው ደግሞ ሊ ማን-ሂ (Lee Man-Hee) የተባለ ግለሰብ ንወ። እንግዲህ ይህ ግለሰብ በደቡብ ኮርያ ብቻ ከ 200,000 በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን በ Korea domain line church ወይንም በቀደምት ጉምቱ የወንጌላውያን አማኞች የተወገዘና ትምህርቱ በቀጥታ የስህተትና የምንፍቅና እንደሆነ የተተቸ ትምህርት ሆኖ እናገኘዋለን።

የትህምርቱ ዋና ገጽታም ከታረደው በግ ከክርስቶስ ውጪ ማዕከልነቱን ወደ ምንፍቅናው ደራሲ ወደ ሊ ማን-ሂ ያደላ መሆኑ በግልጽ ከትምህርቶቹና ከአቋሞቹ መረዳት ይቻላል።

ይህ ሰው (ሊ ማን-ሂ) ራሱን ዳግም የተገለጠ ሐዋርያው ዮሐንስ እንደሆነ በግልጽ የሚያስተምርና የራሱንም የታደሰና እንደሚመቸው አድርጎ የተስተካከለ መጽሀፍ ቅዱስ (በተለይ በዮሐንስ ራዕይ ላይ) እስከ ማሳተም የደረሰ በቅዱስ ቃሉ ስልጣን ላይ የተዳፈረ ሰው ነው።

ለዚህም በማሳያነት ራሱን ዳግም የተገለጠ ዮሐንስ (አዲሱ ዮሐንስ) አድርጎ ከመቁጠሩ ጋር በተያያዘ ዮሐንስ ራዕይ ዳግም በሙላት ተገልጦልኛል በማለትና በዮሐንስ ራዕይ 1 - 3 ያሉት በእስያ ያሉት ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት የእስያ ሳይሆኑ በኮርያ ለሚገኙ ከተሞች ናቸው ማለት አስተካክሎ የራሱን መጽሀፍ ቅዱስ አስትሟል። ያም ከተማ በዋናነት Gwa-Cheon የምትባል ለሰሜን ኮርያ የቀረበች ከተማ ስትሆን የአስተምህሮ ተቋሙ ዋና መቀመጫ ናት።

ትምህርቶቹ በጥቂቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከሰውዬው ማንነት አንጻር

1. ከላይ እንደተገለጸው ሊ ማን-ሂ ራሱን ሐዋርያው ዮሐንስ መሆኑን ያስተምራል ወይንም አዲሱ ዮሐንስ እያለ ራሱን ያቆላምጣል (Fact 52)

  • ይህ ትምህርት ፈጽሞ በክርስትና አስተምህሮ ውስጥ የሌለና ሰዎች ዳግም ሌላ ሰው ሆኖ ይወለዳሉ ለሚለው የህንድ(ሁድሃ)፣ የጥንት ቻይናና፣ የጥንት ግሪኮች ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ የዳግም ስጋ ውልደት ትርክት ነው።

2. ሊ ማን-ሂ አዲሱ ዮሐንስ ነኝ እንደማለቱ የዮሐንስ ራዕይን "እውነታ" እንደተቀበለ ያስተምራል (Fact 43, Exposition III-2, 71) ይህም ልክ አይደለም ብሎ ያመነበትን የዮሐንስ ራዕይ ክፍል እንዲያወጣና በራሱ ሃሳብ እንዲተካ ነጻነትን ለራሱ አጎናጽፎታል።

  • ይህ ሰው ዘርፈ ብዙ ስህተቶች የሚታይበት ቢሆንም የቃሉን ስልጣን የዳሰበት ግን ሰፊውን ድርሻ ይይዛል። ራዕይ መጽሐፍን ራሱ ራዕም መጽሐፉ ማንም እንዳይጨምርበትም ሆነ እንዳይቀንስበት ቆልፎ ያስቀመጠና ማንም ልሰርዝ ልደልዝ ቢል እግዚአብሔር የተገለጹትን እርግማኖች ኣንደሚያወርድበት ቢናገርም ይህ ሰው ይህንን በመተላለፍ አያሌ ስህተቶችን በመጽሐፉ ላይ ሲሰራ እናገኘዋለን። የዚህም ነገር መጨረሻ ጥፋት መሆኑ ከማንም ያልተሰወረ ሀቅ ነው።

3. በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 2፥26-27 ላይ የተገለጸውና ሕዝቡን በብረት በትር ይገዛል የተባለው ለእርሱ (ሊ ማን-ሂ) የተጻፈ ቃል እንደሆነ ያስተምራል።

  • ክፍሉ ድል ለሚነሳው ተብሎ ለትያጥሮን የተጻፈውን ቃል እንደፈለገ ለራሱ ፍላጎት ለመተርጎም የሚታትር ግልብ ሀሳኢ መሆኑን እንረዳለን።

4. በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 12፥1-9 ባለው ክፍል ላይ የተገለጸችው ሴት ታሪክ ከሴቲቱ የተወለደውና(ቁ5) ዘንዶው ሊውጠው በተዘጋጀ ጊዜ(ቁ4) ወደ እግዚአብሔር ዙፋን የተነጠቀው(ቁ5) የያኔው ህጻን ያሁኑ ሊ ማን-ሂ መሆኑን በድፍረትና ያለ ምንም ፈሪሃ እንግዚአብሔርም ሆነ አክብሮተ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል።

  • ይህ ሰው በአጭር አገላለጽ በ 2ጴጥ 1:20 ያለውን "ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤" የሚለውን ክፍል ወይ አላነበበውም አልያም ሊቀበለው አልፈቀደም ማለት ነው።

5. የእርሱ (ሊ ማን-ሂ) ንግግር አጽናኝና የመንፈስ ቅዱስ ቃል መሆኑን ይናገራል (Exposition 18)

  • በርግጥ ቃሉ እኛ እግዚአብሔር እኛን ባጽናናበት መጽናናት ሌሎችን እንደምናጽናና ይገልጻል (2ቆሮ 1:4) ይሁንና ግን አጽናኝ ተብሎ የተገለጸው የየትኛውም የሰው ልጅ የሌለና ክርስቶስ ራሱ የመሰከረለት ቅዱስ መንፈሱ ብቻ መሆኑን እንረዳለን።(ዮሐ 14:15-16, 26, 15:26) በዚህም ይህ ሰው የመንፈስ ቅዱስን ድርሻ ለመውሰድ ያልፈራና ራሱን በመንፈስ ቅዱስ ስፍራ ያስቀመጠ ደፋር አስተማሪ ሆኖ እናገኘዋለን።

ከድኅነት(Salvation) አንጻር

ይህ ሰው ከድኅነት አንጻር ራሱን በወንጌሉና በክርስቶስ ስፍራ ያስቀመጠ ራሱን የመዳን መንገድ አድርጎ የሚቆጥር ሰው ነው። ለአበይትም ከንግግሮቹ ከተወሰዱት መካከል፦

  1. ዘፍ 2:9 ላይ የተቀመጠው የሕይወት ዛፍ በመባል የተገለጠው ሕይወት ሰጪ ራሱ ሊ ማን-ሂ መሆኑን ያስተምራል (Exposition 57) ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሊ ማን-ሂ ራሱን የእግዚአብሔር መንግስት የሕይወት ዛፍ እያለም ይጠራል (Exposition 11, 57)
  2. ከ ሊ ማን-ሂ ውጪ መዳን፣ ዘላለማዊ ሕይወትም ሆነ መንግስተ ሰማይ አለመኖሩን በግልጽ ያለ አንዳች መስቀቅ ያስተምራል። (Exposition 195)
  3. በክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ጊዜ ጻድቅ የሆነውና የሚድነው አሁን ክርስቶስ "በመንፈስ" እንደመጣ (Already come) የሚያምን ብቻ ነው ይላል። (Exposition III-2, 26)
  • ይህ ትምህርት የክርስቶክ ምፅዓት ከሆነ ዕንደቆየና አሁን የምንጠብቀው ክርስቶስ እንደሌለ መናስተማር አማኞችን የጌታቸውን መምጣት ከመናፈቅ እንዲናጥቡ የሚያደርግ ሲሆን አሁን ክርስቶስ መጥቶ በኮርያ ውስጥ እንደሚገኝ ለሚያስተምሩት ትምህርት መሰረትን ያስጥልላቸዋል።
  • ክርስቶስ ሲመጣ እንዲህ በድብቅ ሳይሆን በግልጽና በገሀድ የወጉት ሁሉ እያዩት(ራዕይ 1:7) በታላቅ ክብር በታላቅ ክብርና በመላዕ አጀብ እንደሚመጣ(1ተሰ 4:16)፤ የመምጣቱም ቀን እንዳሁኑ መንደላቀቅና አለማዊ አትኩሮት ባለበት እየቀጠለ ሳይሆን ላላመኑበት ታላቅ ጭንቅና ተራሮች ሆይ ውደቁብን የሚያሰኝ የታላቅ ምጥ ቀን መሆኑን ቃሉ ያስተምረናል።(1ተሰ 5:3)

4. በክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ጊዜ ሊ ማን-ሂ እውነት፣ ሕይወትና መንገድ እንደሚሆን በድፍረት ያስተምራል (Exposition III-2, 11)

  • የዚህ ሰው ድፍረት ልክ ያጣና ክርስቶስ ራሱን "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" ዮሐ 14:6 ብሎ የገለጸበትን ሃሳብ የመዳን ብቸኛ መንገድነቱንና አዳኝነቱን ያሳየበትን ሃሳብ ይህ ሰው እንደቀላል ሲዘርፍና ለራሱ ስም ሲለጥፍበት የማይፈራ ሰው ነው። በዚህም ራሱን ከክርስቶስ ጋር ለማላከክ የሞከረ አስተምሮን የያዘ ነው።

ከቤተ ዕምነት አንጻር

  1. በደምሳሳው የኦርቶዶስ፣ የኦርቶዶስ ፕሮቴስታንት ኣንዲሁም የፕቶቴስታንት አስተማሪዎች ለሰይጣን የተገቡ (Belongs to Devil) እንደሆኑ ያስተምራል (Exposition 297)
  2. በተጨማሪም በዮሐንስ ራዕይ 14፥1፣3 ላይ የምናገኘው በጽዮን ተራራ ስለተሰበሰቡት ከ አስራ ሁለቱ ነገዶች የተውጣቱ 144 ሺህ ሰዎች የሚናገረውን ሃሳብ ኣነዚህ 144 ሺህ ሰዎች የእርሱ ተከታዮች አልያም የ Schincheonji አስራ ሁለት ነገዶች ኣንደሆኑና እነርሱም የቅዱስ ሕዝብና የንጉስ ካህናቶች "እንደሚሆኑ" ያስተምራል። (Exposition III-1, 193, 4)
  • ይህ ክፍል ከምድር ሁሉ ስለተዋጁና በጉን የሚከተሉ ሲሆኑ ለዚህ ምርጫ እንደመስፈርትነት የቀረበው ውሸት በአፋቸው አለመገኘቱ፣ ከሴት ጋር አለመተኛታቸው፣ ነውር ያልተገኘባቸው መሆናቸውና የመሳሰሉት እንጂ ፈጽሞ የ Shincheonji አባልነት በራዕዩ ላይ ቀርቦ አናገኝም። ይህ ፍጹም የእግዚአብሔርን ምርጫ ብቻ የምናይበት ክፍል ነው።
  • በተጨማሪም ከንጉስ ካህንነት አንጻር ያነሳው ሃሳብ በ 2ጴጥ 2፥9 ላይ "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤" የተገለጠ ሃሳብ ሲሆን እርሱ ለዚህ መስፈርትነት ያነሳው የ Shincheunji አባልነት በቃሉ ውስጥ የሌለና ከዛ ይልቅ እንደውም የንጉስ ካህንነት ጉዳይ እንደርሱ አገላለጽ የተስፋ(የወደፊት) ጉዳይ ሳይሆን በአማኞች ሕይወት የተከናወነ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለ።

3. ከዚህ በተጨማሪም የነዚህ የShincheonji አስራ ሁለት ነገድና 144 ሺህ አባል ለመሆን በሊ ማን-ሂ የሚዘጋጅ 300 ጥያቄዎችን የያዘ ፈተና ማለፍ ግዴታ ሲሆን ፈተናውን ያለፉት ብቻ የነገዱ አባል እንደሚሆኑ ያስተምራል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህንን ፈተና መመለስ የሚችሉት የ Shincheonji አባላት ብቻ መሆናቸውንና ከዛ ውጪ ያሉ ሰዎች ቢፈተኑ እንኳን መመለስ እንደማይችሉ የእግዚአብሔር ማጣሪያ ወንፊት የርሱ የወረቀት ፈተና እንደሆነ አድርጎ አባላቱን ያስተምራቸውል።

  • ይህ ፈጽሞ ስህተት የሆነና እኛ ድኅነትን ያገኘነው እንዲሁ በጸጋ መሆኑን ቅዱስ ቃሉ በማያወላዳ ሁኔታ አስረግጦ ያስተምረናል። (ቆላ1:13-14፣ ዮሐ3:16፣ ኤፌ 2፥9. . . ) የዳንነው በጸጋ ብቻ ነው!

ከቃሉ ባለስልጣንነት አንጻር

ለዚህ ሀሳብ ከላይ ያየናቸው ሃሳቦች ብቻ በቂ ሲሆኑ የቅዱስ ቃሉን ስልጣን በመዳፈርና በመጋፋት ቃሉን ለራሱ ጥቅምና ሃሳብ ብቻ እየተረጎመ ከመገኘቱም በላይ መጽሐፍ ቅዱስን ዳግም ለማስተካከል በድፍረት የተነሳ ሰው ነው። በዚህም ከቦታ ስም እስከ ጭብጥ ለውጥ ድረስ በማድረቅ ለራሱ የሚመቸውን ትርጓሜ ሰጥቶ የሚያስተምር ሰው ነው።

ማስታወሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ የተነሳሳነው የዚህ የአስተምህሮ ቡድን በዚህ ወቅት በከተማችን አያሌ ቦታዎች በከባድ ፍጥነት እየተንቀሳቀሰ ያለ በመሆኑና አቀራረባቸውና ትምህርታቸው ለምድ ለባሽ ተኩላ እንደሚባለው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አሳበው ይህንን ፍጹም ከቃሉ ያፈነገጠ ይምህርት በቀስታ የሚያሰርፁ የገንፎ ውስጥ ስንጥር የጭቃ ውስጥ እሾህ የሆኑ ቡድኖች ናቸው።

በዚህ ጊዜ በአብዛናው በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ኮሌጅና ዩኒቨርስቲዎች ደጃፍ የማይጠፉ ሆነዋል። እነዚህ ቡድኖች በዋናነት ክርስቲያን(ፕሮቴስታንት) የሚያድኑ(Hunt) ሲሆን በምንም መልኩ የጠለቀ ስነመለኮታዊ ውይይቶችን የማያደርጉና ሃሳቡ ሲነሳም ካዘጋጁት ትምህርት በኋላ እንደሚደርስ አድርገው በማድበስበስ በማለፍ ይታወቃሉ።

ተወዳጆቻችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተባለበት ስፍራ ሁሉ መገኘት መንፈሳዊነት አይደለምና ነገሮችን በማስተዋል ልታደርጉ እንደሚገባ አሳስበን ማለፍ እንወዳለን።

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ኤፌ 4:14

ለተጨማሪና ለበለጠ መረጃ በ @BenChabod ሊያነጋግሩንና ግብአቶችን ማድረስ እንችላለን። እንዲሁም www.21church.com ላይ ስለ ትምህርቱ የበለጠ ማግኘት ይችላሉ።[1]

በናሆም ሙሉነህ ተጻፈ


ተጨማሪ

በመዲናችን አዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ክርስትና ባዕድ የሆነ ‹አዲስ ሃይማኖት› የሚሰብክ አንድ ድብቅ ቡድን እንቅስቃሴውን ከጀመረ ድፍን አንድ አመት አለፈ፡፡ ይህ ቡድን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴውን የሚከውነው በድብቅ ነው፡፡ የዚህ ሃይማኖታዊ ቡድን ቀዳሚ ትኩረት በወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶች ናቸው፡፡ ቡድኑ በመዲናችን አዲስ አበባ ለትራንስፖርት አማካኝ ናቸው በሚል በተመረጡ ቦታዎች ለምሳሌ በሜክሶኮ ኮሜርስ፣ በብሔራዊ ስታዲየምና በመገናኛ አከባዎች የማስተማሪያና የአምልኮ ስፍራ አዘጋጅቶ ብዙ ታዳጊ ወጣቶችንና ወጣቶችን በትምህርቱና በአምልኮው እያጠመቀ ይገኛል፡፡ ይህ ቡድን ሀገር በቀል ቡድን አይደለም፡፡ የቡድኑ መነሾ ደቡብ ኮሪያ የሚገኘው “shincheonji church of Jesus the Temple of Tabernacle of the Testimony” ነው፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛው የቡድኑ አባላት ከደቡብ ኮሪያ የመጡ ኮሪያዊያን ናቸው፡፡

ቡድኑ እራሱን ‹shincheonji› ብሎ አያስተዋውቅም፡፡ ‹shincheonji› በኮሪያኛ ‹አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ማለት ነው፡፡ የቡድኑ አባላት እራሳቸውን ‹shincheonji› በሚል መጠሪያ ማስተዋወቅ የማይፈልጉበት ብቸኛ ምክንያት ሰዎች ‹shincheonji› መሆናቸውን ካወቁ መናፍቅ/cult በሚል ተቃውሞ እንቅስቃሴያው እንዳይገታ ስለሚሰጉ ነው፡፡ ስለዚህም የቡድኑ አባላት ሰዎችን ወደዚህ ቡድን ሲጋብዙ የኮሪያዊያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን/Korean Bible Study Group የሚለውን መጠሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ይህም ቀዳሚው የቡድኑ ዘዴ መሆኑን አንባቢው ልብ ይበል፡፡ የቡድኑ አባላት አዳዲስ ሰዎችን ለማጥመድ ይችሉ ዘንድ ህዝብ በሚበዛባቸውን ባዛሮች፣ ቤተ-ክርስቲያንናት፣ ኮንፍራንስ በሚካሄድባቸው የስብሰባ አዳራሾች፣ በሀገራዊ ሰልፎችና በመሳሰሉ ስፍራዎች ላይ በማተኮር ማራኪ በሆነ አቀራረብ (Communication) ተጠቅመው የሚያጠምዱዋችን ሰዎች የኮሪያዊያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድንን/Korean Bible Study Group ይታደሙ ዘንድ በመጋበዝ አድራሻ ይለዋወጣሉ፡፡ ይህም ሁለተኛው የቡድኑ ዘዴ መሆኑን አንባቢው ልብ ይበል፡፡ ከዚህ በፊት ከነበረው ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው ለእነዚህ ቡድኖች አዎንታዊ መልስ ሲሰጡ የሚታዩት ለመጽሐፍ ቅዱስ የጥናት ባህል አዲስ ያልሆኑ የወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት ታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶች ናቸው፡፡ እስካሁን ባለኝ መረጃ ይህ ቡድን በእንዲህ አይነቱ ስልት ያጠመዳቸውን ከ20 እስከ 30 የሚያህሉ ታዳጊ ወጣቶችንና ወጣቶችን ለ1 አመት በሚዘልቅ የመጀረመሪያ ዙር ስልጠና አስተሮ ሊያስመርቅ 2ና 3 ወራት ቀርተውታል፡፡ ምንም እንኩዋን ቡድኑ የመጀመሪያውን ዙር ተማሪዎች ከጥቂት ወራት በኃላ ሊያስመርቅ ቢዘጋጅም ከመጀመሪያው ዙር ቀጥሎ እያንዳንዱ ከ40 እስከ 50 የሚያህል ታዳጊ ወጣቶችንና ወጣቶችን የያዘ ባለ 3 ዙር ቡድን እያስተማረ ይገኛል፡፡ ከረዕቡና ከቅዳሜ ወጪ ለ5 ቀናት ከ3 ፈረቃዎች (ጠዋት ከሰዓትና ማታ) መካከል ተማሪው የሚመቸውን ፈረቃ መርጦ ሲያበቃ ለተከታታይ ቀናት ለ1 አመት የጊዜ ርዝማኔ በእንግሊዘኛ የማስተማሪያ ቁዋንቁዋ ተጠቅመው በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡

የቡድኑ አባላት ከወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት አያያዝ የሚለያቸው ነገር ቢኖር የሚያስተምሩዋቸውን ታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶችን የስልክ አድራሻ በመውሰድ በየቀኑ ስለ ተማሩት ትምህርት አስመልክቶ የሚሰማቸውን ማንኛውንም ስሜት ለማድመጥ ዘወትር ምሽት የሞባይል መልዕክት /SMS/ እየላኩ በጥሞና  የሚከታተሉ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህም ሶስተኛው የቡድኑ ዘዴ መሆኑን አንባቢው ልብ ይበል፡፡

የ1 አመቱ የትምህርት መርሃ-ግብር ወደ 58 የሚጠጉ ርዕሰ-ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን እያንዳንዱ ርዕሰ-ጉዳይ እርስ በእርስ በእጅጉ የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን ቀጥሎ ያለው ግልጽ ይሆን ዘንድ አስቀድሞ የመጣው ቀጥሎ ለሚመጣው እንደ መሰረት ሆኖ ያገለግላል፡፡ 58ቱም የተሳሰሩት ትምህርቶች ሙሉ ለሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን የሚጠቀሙ እንደመሆናቸው መጠን ተማሪው እራሱን በመንፈሳዊ ስፍራ እንዳስገኘ እንዲሰማው በማድረግ ትምህርቱን በእሺታ እንዲከታተል ሲያደርገው ይታያል፡፡ በመጀመሪያዎቹ የትምህርት ቀናት ተማሪዎች አድራሻ እንዲለዋወጡ አይፈቀድም፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት ምናልባትም ተማሪዎች ማንነታቸውን አውቀው ለሌሎቸ ተማሪዎችን በመንገር እንዳያስቆሙዋቸው ከሚል ስጋት ጋር እንደሚያያዝ ትምህርቱን አቁመው የወጡ የቀድሞ ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ወደ ትምህርቱ ማብቂያ አከባቢ ሲደርሱ አድራሻ እንዲለዋወጡ ብቻ ሳይሆን ከተቻለም እርስ በእርስ ተቀራርበው የፍቅር ግንኙነት በመፍጠር ይጋቡ ዘንድ በግል እስከማበረታታት ይደርሳሉ፡፡ የዚህም ማበረታቻ መሰረታዊ ምክንያት ትምህርቱን ጠንቅቀው የጨረሱና ከቡድኑ ጋር አመልኮ የጀመሩ ተማሪዎች ለቡድኑ ሃይማኖት መስፋፋት ቁልፍ ግለሰቦች መሆናቸውን ከማመን የሚመነጭ መሆኑን መገመት አያዳግትም፡፡ ይህም አራተኛው የቡድኑ ዘዴ መሆኑን አንባቢው ልብ ይበል፡፡ ተማሪዎች ትምህርቱን ሲከታተሉ ቆይተው በ‹shincheonji› ለማመን የማያወላዱበት የትምህርት ደረጃ ደርሰዋል ሲሉ እያንዳንዱን ተማሪ በግል በማግኘት የፋሲካ(Passover) ክንዋኔን እንዲፈጽሙ ያደርጉዋቸል፡፡ የፋሲካ(Passover) ክንዋኔ አብይ አላማ ተማሪው የቡድኑ እውነተኛ ማንነት ‹shincheonji› እንደሆነና እስከዛሬ ሲማር የነበረው ትምህርት ወደ ‹shincheonji› ሃይማኖት ለመቀላቀል እንደሚያስችለው በመግለጽ ተማሪው አሁን ገና እንደ ዳነ ተነግሮት ቀድሞ ህብረት ሲያደርግበት ከነበረው የወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት ተላቅቆ ለአንዴና ለዘላለም ወደ “shincheonji church of Jesus the Temple of Tabernacle of the Testimony” እንዲቀላቀል በመጋበዝ ነው፡፡ ተማሪው ከዚህ ወዲህ በወንጌላዊያን አብያተ-ክርሰቲያናት ተገኝቶ እንዲታደም ሆነ እንዲማር አይፈቀድለትም፡፡ ይልቁንም ቡድኑ ባዘጋጀውና በመዲናችን አዲስ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም አከባቢ በሚገኝ ድብቅ የአምልኮ ስፍራ እንዲቀላቀል ይነገረዋል፡፡ ተማሪውም እሺታውን ሲገልጽ የጺዖን ተራራ (Mount Zion) በሚሉት የድብቅ የአምልኮ ስፍራ ዘወትር እሁድ ከሰዓት ተገኝቶ ከቡድኑ ጋር እንዲያመልክና ማዕድ እንዲቆረስ ይሆናል፡፡ የአምለኮ-ስርዓቱ የሚፈጸመው ለአምለኮ የመጣው ተማሪ በጾታ ተከፍሎ በተዘጋጀው የልብስ መቀየሪያ ክፍል ገብቶ ሲያበቃ ልብሱንና ጫማውን በመቀየር የተዘጋጀለትን ሙሉ ነጭ ልብስ ለብሶ ወደ ማምለኪያው ስፍራ ይመጣል፡፡ ተማሪው ወደ ማዕከላዊው የአምልኮ ስፍራ በመቅረብ የዮጋ ልምምድ የሚያደርጉ ሰዎች እንደሚቀመጡት እግሩን በእግሩ ላይ አነባብሮ በማስቀመጥ አይኑን በመጨፈን ቆሞ የሚሰብከውን አልያም የሚያወራውን የቡድኑ አባል ስብከት በአዝነ-ህሊናው (Imagination) እያብሰለሰለ ይሰማል፡፡ በእዚህ ስፍራ የተገኙ ታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶች የቡድኑ አባላትን ጨምሮ ሁሉም ነጫጭ ልብስ ለብሰው ክብ በመስራት ይህንን ክንዋኔ ዘወትር ሰንበት ከሰአት ይፈጽማሉ፡፡ የአምልኮ መርሃ-ግብሩ ሲያበቃ የታደሙት ሁሉ የተዘጋጀውን ማዕድ በጋራ ተቆዋድሰው ይለያያሉ፡፡ ማዕዱ በዋናነት የኮሪያዊያን ምግብ የሚበዛው ቢሆንም የሀበሻ ምግብም አይጠፋውም፡፡ እንግዲህ በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፈ ተማሪ ዘወትር እሁድ ከሰዓት የሚደረገውን አምለኮ እየፈጸመ የቡድኑን ትምህርት ተከታትሎ ሲጨርስ ልክ የቡድኑ አባላት ሰዎችን ለማጥመድ ህዝብ በሚበዛበት አከባቢ በመሄድ ብዙዎችን ጋብዘው እንደሚያመጡ እነዚህም ምሩቃን ተማሪዎች ይህንኑ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር ምሩቃኑ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን እንደመሆናቸው መጠን ሃይማኖቱ በተሳለጠ ሁኔታ እየተስፋፋ እንዲሄድ ምሩቃኑ የተወሰነ ስልጠና ተሰጥቶዋቸው የተማሩትን ትምህርት ለአዳዲስ ገቢዎች እንዲያስተምሩ አስተማሪ ሆነው ይሾማሉ፡፡  በሀሰት ተጠምደው፣ በሀሰት የተጠመቁና በሀሰት የሚያመልኩ ምስኪን ወንድሞችና እህቶች ሳያውቁ ሌሎችን በሀሰት የሚያጠምዱ የሀሰት መምህራን ሆነው ይሾማሉ፡፡

የ ‹shincheonji› ሃይማኖት የብሉይ ኪዳኑን የህዝበ-እስራኤል 12 ነገዶች እንዲሁም የኢየሱስን 12 ደቀ-መዛሙርት ምሳሌ በማድረግ በሊ. ማን. ሂ(Lee Man-hee) ማዕከላዊነት ተፈጥሮ በ12 ነገዶች የተደራጀ ሃይማኖት ነው፡፡ እነዚህ 12 ነገዶች በ12ቱ የጌታ ኢየሱስ ሐዋሪያት ስም የተሰየሙ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ በሊ. ማን. ሂ(Lee Man-hee) ምሪት የገባው ብቸኛ ነገድ የጴጥሮስ ነገድ ነው፡፡ ይህ ሃይማኖት እንቅስቃሴ አይደለም ሃይማኖት እንጂ፡፡ እንቅስቃሴ በማዕከማዊነት የሚመራው ተዋረዳዊ መዋቅር የሌለው ሲሆን ሃይማኖት ግን ከእንቅስቃሴ በተለየ ሁኔታ ማዕከላዊነትን ተጎናጽፎ ተዋረዳዊ መዋቅር የሚከተል ነው፡፡ በምድረ-ኢትዮጰየያ  የገባው ይህ የ‹shincheonji› cell በደቡብ ኮሪያ ከሚገኘው “shincheonji church of Jesus the Temple of Tabernacle of the Testimony” ከሚባለው ሃይማኖት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው፣ ቀድሞኑም በዚህ ሃይማኖት መሪ አማካኝት ወደዚህ ምድር በሚሲዮናዊነት የተላኩ ግለሰቦችን የያዘና  ማንኛውንም ምሪት  የሚቀበልና ዘወትርም ለዚህ ሃይማኖት መሪ ሪፖርት የሚያደርግ  ህቡዕ/ድብቅ ቡድን ነው፡፡

ይህን ሃይማኖት ከሌሎቹ መናፍቃዊ ሃይማኖቶች ለየት የሚያደርገው ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚልካቸው የሃይማኖቱ ሚሰዮናዊያን መልካም ነው ለሚሉት አላማ ውሸት መናገርን እንደ ትክክልነት አምኖ መቀበሉ ነው፡፡ ለምሳሌ ከውሸቶቹ መካከል፡-

ሀ) የቡድኑ አባላት መጀመሪያ የሚናገሩት ስም የውሸት ስም መሆኑ፤ (እውነተኛ ስማቸውን  ‹shincheonji› መሆኑን የሚናገሩት ተማሪዎቹ ትምህርቱን የማይተውበት ደረጃ ደርሰዋል ብለው ሲያምኑ ብቻ ነው)

ለ) የተላኩት ከ ‹shincheonji church of Jesus the Temple of Tabernacle of the Testimony”  ሆኖ ሳለ የመጡት ሆነ አባል የሆኑበት ቤተ-ክርስቲያን በኮሪያ ውስጥ የሚገኝ የፕርስፒቴሪያን ቤተ-ክርስቲያን መሆኑን መናገራቸው፤

ሐ) በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት ህጋዊ ፈቃድ መንግስት እንደ ሰጣቸው መናገራቸው፤

መ) የተመረቁ ተማሪዎችን ለአስተማሪነት ሲያሰለጥኑ አዳዲስ ተማሪዎችን እንዴት ዋሽቶ ማሳመን እንደሚቻል ማስተማራቸው፤

ሠ) በልማት አልያም በበጎ ፈቃድ ድርጅት ስም በመግባት በድብቅ ይህንን እንቅስቃሴ ማሳለጣቸው፤

ከሁሉ በላይ ደግሞ የቤተ-ክርስቲያን ፈቃድ ካወጡ የሀገር ውስጥ ሌባና ወመኔ ‹መጋቢያን› ጋር ተመሳጥረው የቤተ-ክርስቲያን ህጋዊ ፈቃድ በየወሩ በመከራየት በኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየት መሞከራቸው የሚያስደነግጠው አካሄዳቸው ነው፡፡ ለመንጋው የማይገዳቸው ነገር ግን የቤተ-ክርስቲያን ፈቃድ አውጥተው ሲያበቁ ለእነዚህ የሃይማኖት ቡድኖች ህጋዊ ground በመስጠት የቤተ-ክርስቲያን ፈቃዳቸውን እያከራዩ ከርሳም ሆዳቸውን የሚሞሉ ሌባና ወመኔ ‹መጋቢያን› መኖራቸው ደግሞ በእጅጉ ያስደነግጣል፡፡ የእነዚህን ሌባና ወመኔ ‹መጋቢያን› ስምና ከመንግስት የቤተ-ክርስቲያን ፈቃድ የተቀበሉትን የቤተ-ክርስቲያን ስም ባውቅም እዚህ ቦታ መጥቀሱ አስፈላጊ ስላልሆነ አልፈዋለሁ፡፡ እዚህ ሌባና ወመኔ ‹መጋቢያ› የቤተ-ክርስቲያንን ፈቃድ እንደ ገንዘብ ማግኛ ዘዴ በመጠቀም በየወሩ የኪራዩን መጠን በመጨመር ቅልጥ ያለ ውንብድና ውስጥ ገብተዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ከኮሪያ ለመጣው መናፍቃዊ ቡድን አስጨናቂ እየሆነ በመምጣቱ ቡድኑ ሌላ በምድረ-ኢትዮጵያ በመቆየት ለዚህ መናፍቃዊ ሃይማኖት ብዙዎችን ለማስገዛት አንድ ዘዴ የዘየደ ይመስላል፡፡ ይህም ዘዴ የተመረቁ አልያም የሚመረቁ ተማሪዎችን በማግባባት በድብቅ የ“shincheonji church of Jesus the Temple of Tabernacle of the Testimony” ቅርንጫፍ የሆነ ሀገር-በቀል ቤተ-ክርስቲያን መመስረት ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ አሁን ባለው ህግ መሰረት 1000 የታደሰ የአባላት መታወቂያ የሚያስፈልግ እንደመሆኑ መጠን 1000ዉን የታደሰ መታወቂያ ከሌባና ወመኔ ‹መጋቢያ› ጋር በገንዘብ በመደራደር ተቀብለው ሲያበቁ በተማሪዎቹ ጠያቂነት መንግስት የሚጠይቀውን የቤተ-ክርስቲያን ቅድመ-ሁኔታ አሙዋልተው ቤተ-ክርስቲያኒቱ እንድትመሰረት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ ይህን ለማድረግ ብዙ ጊዜ የሚፈጅባቸው አይመስለኝም፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተማሪዎቹ ኢትዮጵያዊ እንደመሆናቸው መጠን ፈቃዱን ለማውጣት አዳጋች ባለመሆኑ ነው፡፡ ያኔ እነዚህ ሰዎች ይህች ቤተ-ክርስቲያን በምታቀርበው ግብዣ በሚሲዮናዊነት ስም በምድረ-ኢትዮጵያ ለመመላለስ የሚቸግራቸው አይሆንም፡፡

ቡድኑ የቆመለት ሃይማኖት ይህንን ሁሉ ሸፍጠኛ አካሄድ ሲከተል ውሸት መሆኑ ጠፍቶት አይደለም፡፡ ይልቁንም በውሸት መልካም ስራ መስራት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡ እኔ እስካለኝ መረጃ የሃይማኖቱ መስራች ወደ ኢትዮጵያ በተለያዩ የሰላምና የእርቅ እንዲሁም በግብረ-ሰናይ ጉዳዮች ዙሪያ መጥቶ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በተያዩ ጊዜያት ውይይት ማድረጉን አውቃለሁ(ለምሳሌ የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ)። በኢትዮጵያ እየሰራ ያለው ይህ ቡድን አባላቱን 1000 ማድረግ ከቻለና የቤተ-ክርስቲያን ፈቃድ ካገኙ የሃይማኖቱ መስራች በቀጥታ ወደዚህ ሀገር የሚመጣ ይሆናል፡፡

ይህ ቡድን የቆመለት ሃይማኖት የአስተምህሮ ምንፍቅና ብቻ ሳይሆን እራሱን የቻለ ሃይማኖታዊ ልማድ(rituals) ያሉት እንደመሆኑ መጠን ተማሪዎች ይህን ሃይማኖት አንዴ ከተቀበሉ በኃላ በልዑል እግዘአብሔር ተአምራዊ እጅ ካልሆነ በቀር በቀላሉ መላቀቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ የነበሩና ቶሎ የወጡ እንዲሁም እየተማሩ ያሉ ወንድሞችና እህቶች እንደሚናገሩት ከሆነ በሃይማኖቱ ለብዙ ወራት የተከተተባቸው የክፋት ዘር በቀላሉ ሊላቀቃቸው ባለመቻሉ ምክንያት አንዳንዶቹ ቁጭ ብለው አልያም ተረጋግተው ማውራት ሆነ መወያየት እስከማይቻላቸው ድረስ ሊነገር በማይችል ጭንቀት ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ ይህ ግነታዊ ጽሁፍ አይደለም፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ ስማቸውን መጥቀስ የማይገባኝ በቅርብ የማውቃቸው አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች በከፍተኛ የአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

አንዳንድ ትጉ ወንድሞች ከዚህ ትምህርት በመውጣት ትምህርቱን ለመጋፈጥ ይችሉ ዘንድ በቡድን ሆነው በጸሎትና በትጋት እንዳሉ አውቃለሁ። ይህን ሁሉ ሲጥሩ ግን የሚረዳቸው የለም። ጨርሶ! ከዚህ ቀደም እንደጻፍኩት የወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት ህብረት ጋር እንኳን ቀርበው እርዱን ቢሉ በእጃቸው ያለውን ሰነድ ከመነጠቅ (መነጠቅ ልበለው እንጂ) በቀር ምንም አልፈየዱላቸውም። ይህም  ህብረቱ ለአመት በአላት ክንዋኔ እንጂ ብዙዎችን ከጥፋት ለመታደግ እንዳልቆመ አስረድቶኛል።

ትምህርቱ ሙሉ ለሙሉ የተማሪዎቹን አዕምሮ የሚቆጣጠር ከመሆኑ በላይ የወንጌላዊያን ቤተ-ክርስቲያናትን ጋለሞታ፣ ጨለማ አድርገው የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ ስዚህም ተማሪዎች ከዚህ ህብረት ቢወጡ እንኩዋን ከገባባቸው ትምህርት የተነሳ ወደ ቤተ-ክርስቲያን ለመሄድ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን በግል ለማንበብ ይቸገራሉ፡፡

የዚህ ቡድን ዋና ትምህርት በራእይ መጽሐፍ ላይ የተመሰረተ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች ብዙ ለመግፋት ባልችልም የዚህን ሃይማኖት የትምህርት ምንነት ለማወቅ ኮሜሪስ በሚገኘው የስልጠና ስፍራ ተመዝግቤ የተወሰኑ የትምህርት መርሃ-ግብሮችን ለመታደም ሞክሪያለሁ።

ታዳጊ ወጣቶቻችና ወጣቶቻችን አደጋ ላይ ናቸው....

በ #Eyosias_Eyoael_Dewo የተጻፈ