Jump to content

ድፋትቅናት

ከውክፔዲያ
(ከ~ የተዛወረ)

ድፋትቅናት (~) በዘመናዊ ላቲን ጽሕፈት የሚታይ ምልክት ሲሆን እንደ ሀበሻ ምልክት ድፋት ይመስላል። ስሙም በእስፓንኛና በተረፉት የአውሮፓ ቋንቋዎች ቲልዴ ሲሆን ይሄ መጠሪያ የተወረሰው ከሮማይስጥ «titulus» /ቲቱሉስ/ («አርዕስት») ሆነ። ምልክቱ ለራሱ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። እንዲሁም ከሌላ ፊደል በላይ ሲታይ የድምጽ ለውጥ ሊወክል ይችላል፤ ለምሳሌ በእስፓንኛ ፊደሉ «Ñ፣ ñ» (/ኝ/) የደረሰው ከ «N, n» (/ን/) ጋር ድፋትቅናትን በመጨመር ነበር።