ላቲን ጽሕፈት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የላቲን ጽሕፈት አሁን የተጠቀመባቸው አገራት

ላቲን ጽሕፈት እንደ ላቲን አልፋቤት ተራ 26 ፊደላት ያህል የጠቀሙት አልፋቤቶች ጽሕፈት ዘዴ ነው። በነዚህ ፊደል ምልክቶች ስብስብ በጋራ የጠቀሙት አልፋቤቶች ስብሰባ ነው። ለምሳሌ የላቲን አልፋቤት ለሮማይስጥ (ወይም «ላቲን») ከመሆኑ በላይ፣ የጣልኛ አልፋቤትየእስፓንኛ አልፋቤትየፈረንሳይኛ አልፋቤትየእንግሊዝኛ አልፋቤት ወዘተ. ሁላቸው የላቲን ጽሕፈት አይነቶች ናቸው፣ ሁላቸውም በላቲን ጽሕፈት ይጻፋሉ። ከነዚህ በላይ በአለም ዙሪያ አሁን አብዛኞቹ ልሳናት በላቲን ጽሕፈት ነው የሚጻፉ።

እንዲሁም ዓለም አቀፍ ድምጻዊ አልፋቤት (IPA) በላቲን ጽሕፈት ፊደላት ላይ ይመሠረታል።

የላቲን ጽሕፈት 26 መሠረታዊ ፊደላት A B C D E F G H I J K L M N O P Q R S T U V W X Y Z ሲሆኑ ለአልፋቤቱ ታሪክ የላቲን አልፋቤትን ይዩ።