A

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

A / aላቲን አልፋቤት መጀመርያው ፊደል ነው።

እንግሊዝኛ የፊደሉ ስም አጠራር /ኧይ/ ሲሆን፣ ይህ ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅን ያንጸባርቃል። ባብዛኛው ቋንቋዎች ግን በተለመደው የአናባቢ «ኣ» ን ድምጽ ኃይል ይወክላል።

ግብፅኛ
ኢሕ
ቅድመ ሴማዊ
አሌፍ
የፊንቄ ጽሕፈት
አሌፍ
የግሪክ ጽሕፈት
አልፋ
ኤትሩስካዊ
A
ላቲን/ኪርሎስ
A
Egyptian hieroglyphic ox head Phoenician aleph Greek alpha Etruscan A Roman A

የ«A» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «አሌፍ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበሬ ራስ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።

በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («እ») ሲሆን፣ በግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኣ» ለማመልከት ተጠቀመ። ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "አልፋ" (Α α) ደረሰ። በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «አ» («አልፍ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «አሌፍ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'A' ዘመድ ሊባል ይችላል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ A የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።