S

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

S / sላቲን አልፋቤት አሥራ ዘጠኘኛው ፊደል ነው።

ቅድመ ሴማዊ
ሺን
የፊንቄ ጽሕፈት
ሺን
የግሪክ ጽሕፈት
ሲግማ
ኤትሩስካዊ
S
ላቲን
S
RomanS-01.png

የ«S» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ሺን» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የጥርስ ስዕል መስለ። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ። በነዚህ ጽሕፈቶች የ«ሽ» ድምጽ ለማመልከት ጠቀመ፤ ይህ ድምጽ ግን በግሪክኛ ስላልኖረ ለ«ስ/ሥ» ይጠቀም ጀመር። ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ሲግማ" (Σ σ) ደረሰ።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ሠ» («ሠውት») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ሺን» ስለ መጣ፣ የላቲን 'S' ዘመድ ሊባል ይችላል።

ትንሹ S[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የትንንሾቹ ላቲን ፊደላት ልማድ ቀስ በቀስ በ400 እና 770 ዓም መካከል ተለማ። በመጀመርያ ግን የትንሹ «S» ቅርጽ እንደ ſ መሰለ። በ1425 ዓም ግድም የኅትመት ማተሚያ ከተፈጠረ በኋላ፣ ትንሹ ቅርጽ «s» በቃል መጨረሻ ብቻ ይታይ ጀመር። ይህ ልማድ የተወሰደው ደግሞ በግሪክኛ እስከ ዛሬ የ«σ» ቅርጽ በቃል መጨረሻ እንደ «ς» መጻፉን ለመምሰል ነበር።

ቀስ በቀስ ይህ «ſ» ጥቅም በኋላ ጠፋና ትንሹ S ምንጊዜም እንደ «s» ይጻፍ ጀመር። ይህ ለውጥ በእስፓንኛ ከ1752 እስከ 1758 ዓም ድረስ ተፈጸመ፤ በፈረንሳይኛ ከ1774 እስከ 1785 ዓም፣ በእንግላንድ ከ1777 እስከ 1816 ዓም፣ በአሜሪካ ከ1787 እስከ 1802 ዓም ድረስ የ«ſ» ጥቅም ከህትመት ጠፋ።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ S የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።