Jump to content

ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት

ከውክፔዲያ

አለም ጽሕፈቶች ወላጅ ሆነው የሚታስቡ 2 ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ተገኝተዋል፣ እነሱም «ጥንታዊ የሲና ጽሕፈት»ና «የዋዲ ኤል ሖል ጽሕፈት» ይባላሉ። «ዋዲ ኤል ሖል» በ1999 እ.ኤ.አ.ግብፅ ተገኝቶ ዕድሜው ከክ.በ. 1800 ዓመት የሚገመት ሲሆን፣ የጥንታዊ ሲና ጽሕፈት በ1904 እ.ኤ.ኣ.ደብረ ሲና በኩል ተገኝቶ ከክ.በ. 1500 ዓመት የተጻፈ ይታመናል።

ጥንታዊ የሲና ጽሕፈት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከሲና ልሣነ ምድር በላይ አሁን ለዚህ ጽሕፈት በርካታ ምሳሌዎች በከነዓን (የዛሬው እስራኤል) ደግሞ ተገኝተዋል። በተለይ የሚታወቀው ደብረ ሲና አጠገብ ካለ አረንጓዴ ፈርጥ ማዕድን ቦታ ነው። ነገር ግን አሁን ከተገኘ ከ100 አመት በኋላ የቋንቋ ሊቃውንት ስለ ተቀረጹት ቃላት ትርጉም በሙሉ እርግጠኛ አይደሉም።

የዋዲ ኤል ሖል ጽሕፈት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የዋዲ ኤል ሖል ጽሕፈት

ይህ ጽሕፈት በግብጽ ውስጥ ተግኝቶ በሴማዊ ሠራተኞች እንደ ተቀረጸ ይታሰባል። የፊደሎቹ ቅርጽ ከግብጽኛ ስዕል ጽሕፈት (ሀይሮግሊፍ) ጋር ተመሳሳይ ነው። እንዲሁም ከጥንታዊ የሲና ጽሕፈት ጋርም ይመሳሰላል። ስለዚህ ሰራተኞቹ ስእሎቹን ተበድረው ከቋንቋቸው ጋር የሚስማማ ድምጽ እንደሰጡት ይታመናል።

ለምሳሌ በጥንታዊ ግብጽኛ ቋንቋ እባብ ማለት «ጀት» ነበር። ስለዚህ በግብጽ ጽሕፈት «ጀ»ን ለማመልከት የእባብ ስዐል ጠቀመ። ነገር ግን በግብጽ ለኖሩት ሴማዊ ሰራተኞችና አገልጋዮች በቋንቋቸው የእባብ ስም በ «ነ» ስለሚጀምር የእባብ ምልክት ከ«ጀ» ወደ «ነ» ተቀየረ።

እንዲሁም ውሃ በግብጽኛ «ነት» ስለነበር የውሃ ምልክት በድምጹ «ነ» ለመጻፍ ስራ ላይ ይውል ነበር። ደግሞ ለሴማውያን የውሀ ስም በ «መ» ስለሚጀምር (ማይ) የውሀ ምልክት በጽህፈታቸው «ነ» ሳይሆን «መ» እንዲሆን ተደረገ።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
F1
አልፍ
O1
Π ቤት
T14
ገምል
O31
ድንት (ድልት)
A28
ሆይ
T3
ዋዌ (ወዌ)
U7
ዘይ
N24
ሐውት
O49
  ጠይት
D36
("ዐ")
የመን (የማን)
D46
("ደ")
ካፍ
S39
ላዊ
N35
("ነ")
ማይ
I10
("ጀ")
ነሐስ
R11
  ሳት
D4
ዐይን
D21
("ረ")
ፈፍ (አፍ)
M22
  ጸደይ
V24
ቆፍ (ቃፍ)
D1
ርእስ
D279
ሠውት
Z9
ታው