Jump to content

ጸደይ

ከውክፔዲያ
ይህ መጣጥፍ ስለ ፊደሉ (ጸ) ነው። ስለ ወራቱ ለመረዳት፣ ፀደይን ይዩ።

ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ ጿ



አቡጊዳ ታሪክ

ጸደይ (ወይም ጸዳይ) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 18ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥሶርያም ፊደሎች 18ኛው ፊደል «ጸዴ» ይባላል። በዓረብኛ ግን ተመሳሳይ ፊደል «ጻድ» አለ።

አማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ «ጸደይ» ከ«ፀፓ» (ፀ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ሣባ ግዕዝ
M22


የጸደይ መነሻ ግልጽ አይደለም። ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ቢታስብም እስካሁን አልተገኝም። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ነኅብ» ነበር። አንዳንድ ሊቃውንት የ«መቃ» ስዕል እንደ ነበር ይገምታል።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ጸዴ ጸዴ צ,ץ ጸዴ


የከነዓን «ጸዴ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ጸዴ» የዓረብኛም «ጻድ» ወለደ። እነዚህ ሁሉ የ«ጸደይ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል።

በተጨማሪ ከ500 ዓክልበ. አስቀድሞ በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤትና በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤት የነበረው ፊደል «ሳን» (Ϻ) ደግሞ የከነዓን «ጸዴ» መጣ። የ«ጽ» ድምጽ ከግሪክኛ ጠፍቶ ስላልተሰማ፣ እንደ ሲግማ (Σ) ለ«ስ» ያሰማ ጀመር። ከ500-400 ዓክልበ. አካባቢ ጀምሮ፣ «ሳን» እንደ ትርፍ ፊደል ተቆጥሮ ተወገደ። ቢሆንም የጠፋው ፊደል Ϻ ከ«ጸ» ጋር ዝምድና አለው።