Jump to content

ቤት (ፊደል)

ከውክፔዲያ

በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧአቡጊዳ ታሪክ

ቤትአቡጊዳ ተራ ሁለተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥሶርያና በዓረብኛ ፊደሎች ሁለተኛው ፊደል «ቤት» ይባላል። በግሪክም ሁለተኛው ፊደል «ቤታ» ይባላል።

በቋንቋ ጥናት የዚሁ ድምፅ ፍች «ነዛሪ የከናፍር ፈንጂ» ይባላል።[1] በዕብራይስጥ አንድ ነጥብ በመሃል ውስጥ ሲኖር () ድምጹ እንደ «ብ» ቢመስልም ያለዚያ ነጥብ ግን (ב) እንደ «ቭ» ይሰማል። ለዚያም ደግሞ በአማርኛ ይህ ድምጽ «ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ» በተለይ በባዕድ ቃላት ሲጋጠም ከ«በ...» ትንሽ ተቀይሯል።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
O1
Π


የቤት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመኖርያ ቤት ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ አጠራሩ ግን «ፐር» ነበር። (ይህም ቃል በ«ፈርዖን» ስም ይታያል።) በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ቤት.. ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ብ.. ሆኖ እንዲሰማ መጣ።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ቤት ቤት ב ቤት


የከነዓን «ቤት» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም «ቤት» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ቤታ.. (Β β) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (B b) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Б, б) እና (В, в) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ቤት» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ሁለት) ከግሪኩ β በመወሰዱ እሱም የ«በ» ዘመድ ነው።

  1. ^ "የግዕዝ መረጃ ከኢኦተቤ ማህበረ ቅዱሳን". Archived from the original on 2014-10-13. በ2015-04-22 የተወሰደ.