ከ«ትሪቶን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
Content deleted Content added
ጥ r2.7.2) (ሎሌ መጨመር: eu:Triton (mitologia) |
Luckas-bot (ውይይት | አስተዋጽኦ) ጥ r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: be-x-old:Трытон (міталёгія) |
||
መስመር፡ 12፦ | መስመር፡ 12፦ | ||
[[ar:ترايتون (ميثولوجيا)]] |
[[ar:ترايتون (ميثولوجيا)]] |
||
[[be:Трытон, бог]] |
[[be:Трытон, бог]] |
||
[[be-x-old:Трытон (міталёгія)]] |
|||
[[bg:Тритон (митология)]] |
[[bg:Тритон (митология)]] |
||
[[bs:Triton (mitologija)]] |
[[bs:Triton (mitologija)]] |
እትም በ09:25, 28 ፌብሩዌሪ 2012
ትሪቶን (ግሪክ፦ Τρίτων) በግሪክ አረመኔ ሃይማኖትና አፈ ታሪክ ዘንድ፣ የውቅያኖስ መልእክተኛ የሆነ አምላክ ነበረ። የፖሠይዶን (የባሕሮች ዋና አምላክ) እና የአምፊትሪቴ ልጅ ይባላል። በትውፊቶቹ እንደሚገለጽ፣ ሰውነቱ ከሆዱ በታች የዓሣ ሲሆን፣ ልዩ የዛጎል ቀንድ ይነፋል።
በአንዳንድ የግሪክ ደራሲ እንደ ፒንዳር፣ ሄሮዶቱስ፣ አፖሎኒዮስ ሮዲዮስ፣ ሉኮፍሮንና ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ ዘንድ፣ ትሪቶን የሊብያ ንጉሥ ሲሆን መኖርያው በትሪቶኒስ ሀይቅ አጠገብ ተገኘ። በዚሁ ሚና ያሶንና አርጎናውቶች በሚባለው አፈታሪክ ይጫወታል።
ጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ (1490 ዓ.ም. የታተመ)፣ ትሪቶን ከካም ልጆች አንዱ ሲሆን በናምሩድ 18ኛው አመት በሊብያ ሠፈረና መጀመርያው የሊብያ ንጉሥ ሆነ፤ ከዚያ በቤሉስ 56ኛው አመት ያኑስ ወደ ሊብያ ደረሰና የትሪቶን ልጅ ሃሞን ተከተለው። በዚህ ዜና መዋዕል አቆጣጠር ትሪቶን በሊብያ የነገሠ ምናልባት ከ2410 እስከ 2315 ዓክልበ. ግድም ነበር።