ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ
Appearance
ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ (ግሪክ፦ Διόδωρος Σικελιώτης /ዲዮዶሮስ ሲከሊዮቴስ/) በ1ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የኖረ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ።
ዲዮዶሮስ በጻፈው የዓለም ታሪክ (50 ዓክልበ. ገደማ) ስለ ኢትዮጵያ (አይቲዮፒያ) መረጃ ይሰጣል። የአባይ ወንዝ መነሻ በኢትዮጵያ ተራሮች ስለ መገኘቱ በብዙ ገጽ ጽፏል። ሜሮዌ የኢትዮጵያ ከተማ ቢሆንም፣ ከሜርዌ በቀር ብዙ ሌሎች አገሮች በ«ኢትዮጵያ» (ከሳሃራ በረሃ ደቡብ ያለው ሁሉ) እንዳሉ ይገልጻል። በፈርዖን 1 ፕሳምቲክ ዘመን (650 ዓክልበ. ገደማ) 200 ሺህ የግብጽ ወታደሮች አገራቸውን ከደው በኢትዮጵያውያን መካከል እንደ ሰፈሩ ይላል። የኒኑስ ንግስት ሰሚራሚስ በጥንት ኢትዮጵያን እንደ ወረረች ይጨምራል። ስለ ኢትዮጵያ ጽሕፈት ሲያብራራ ማለቱ የመርዌ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይመስላል።
በቀይ ባሕር ዳርቻ ወይም በአሁኑ ኤርትራ፣ ጂቡቲና ሶማሊላንድ ውስጥ፣ አንድ «አሣ በል» የሚባል የኢትዮጵያ ብሔር እንደሚኖር ይጽፋል። ደግሞ ሌሎች የኢትዮጵያ (የአፍሪካ) ብሔሮች «ሥር በል»፣ «ፍሬ በል»፣ «ቅጠል በል»፣ «አዳኞች»፤ «ዝሆን በል»፤ ሲሞዌስ፣ «ሰጎን በል»፣ ኩኖሞኔስ እና «ዋሻ አደሮች» ናቸው። ከዚህ የበለጠ ስለ ኢትዮጵያ (ስለ አፍሪካ ከሳሃራ ደቡብ) ሁኔታ በሰፊው ይገልጻል።