Jump to content

ሰሐራ በረሓ

ከውክፔዲያ
(ከሳሃራ በረሃ የተዛወረ)
ናሳ የተነሳ የሰሃራ በርሃ የሳተላይት ፎቶ

ሰሐራ በረሓ (አረብኛ፦ الصحراء الكبرى አል-ኩብራ ወይም ታላቁ በረሓ ማለት ነው።[1]) የዓለማችን ሰፊው ሞቃት በረሓ ነው። በዚህም ስፋቱ ከ9,400,000 ካሬ ኪ.ሜ. (3,630,000 ካሬ ማይል) በላይ ነው። በረሓው የሚሸፍነው አብዛኛውን የሰሜን አፍሪካ ክፍል ሲሆን በስፋቱም ከአውሮፓ ወይም ከአሜሪካ ጋር ይወዳደራል። ከዚህ በረሓ የሚሰፋው ብቸኛው አንታርክቲካ ሲሆን ይህም የሆነው በዝቅተኛ የዝናብ መጠን ነው። የሰሐራ በረሓ የሚያካልለው የሜዲትራኒያን ጠረፍ ጨምሮ ቀይ ባሕርን እስከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጠረፍ ድረስ ያለውን ነው። በስተደቡብሳር ምድር እና የቁጥቋጦ ምድር የሆነውን ከበረሓው ጋር በሚያገናኘው የሳህል መቀነት ያዋስነዋል።
አንዳንዶቹ የአሸዋ ክምሮች እስከ 180 ሜትር (590 ጫማ) ከፍታ አላቸው።[2]

ምዕራብሊቢያ ክፍል የሚገኝ የሰሐራ በርሓ ክፍል

የአየር ሁኔታ ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሰሐራ በረሓ ባለፉት ጥቂት መቶ ሺህ ዓመታት ሲለዋወጥ የቆየ የአየር ሁኔታ ነበረው። በቀዝቃዛው የበረዶ ዘመን ክፍል (glacial period) ጊዜ በረሓው ከዚህም በላይ ሰፊ ነበር። በዚህ ዘመን መጨረሻ (ከ8000 ዓ.ዓ. እስከ 6000 ዓ.ዓ.) አካባቢ በርከት ያለ የዝናብ መጠን ተመዝግቦ ነበር።

አሃገር ተራራ ላይ የሚገኙ የበረሓ ተክሎች እነዚህ በአከባቢው ሕይወትን ለማቆየት ይጠቅማሉ።

የካቲት ፲፩ ቀን 1971 ዓ/ም በአብዛኛው ደቡባዊ አልጀሪያ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ጥሎ ነበር። በዚህ ዕለት ለግማሽ ሰዓት ያህል የቆየ የበረዶ ነጎድጓድ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ በረዶው ጠፍቷል። ይህ ዜና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሓን ለመጀመሪያ ጊዜ በሕይወት የምናስታውሰው ዝናብ ሰሐራ በረሓ ላይ በሚል ርዕስ ሊወጣ ችሏል።


የውጭ ማያያዣዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ http://online.ectaco.co.uk/main.jsp?do=e-services-dictionaries-word_translate1&status=translate&lang1=23&lang2=ar&source_id=2119140 Archived ማርች 9, 2009 at the Wayback Machine |title=English-Arabic online dictionary |publisher=Online.ectaco.co.uk |date=2006-12-28 |accessdate=2010-06-12
  2. ^ Arthur N. Strahler and Alan H. Strahler. (1987) Modern Physical Geography–Third Edition. New York: John Wiley & Sons. Page 347