ከ«3 አመነምሃት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{የንጉሥ መረጃ | ስም = 3 አመነምሃት | ሀገር = ግብጽ | ስዕል=Egypte louvre 231 visage.jpg | የስዕል_መግለጫ = የኒ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 35፦ መስመር፡ 35፦
File:Sphinx Amenemhat3 Budge.jpg |የኒመዓትሬ እስፊንክስ
File:Sphinx Amenemhat3 Budge.jpg |የኒመዓትሬ እስፊንክስ
File:Ägyptisches Museum Berlin 023.jpg|የኒመዓትሬ ምስል
File:Ägyptisches Museum Berlin 023.jpg|የኒመዓትሬ ምስል
File:Amenemhat_III_Louvre.jpg|የኒመዓትሬ ምስል
</gallery>
</gallery>



እትም በ02:36, 6 ሜይ 2014

3 አመነምሃት
የኒመዓትሬ ምስል
የኒመዓትሬ ምስል
ሥርወ-መንግሥት 12ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት 3 ሰኑስረት


ኒመዓትሬ፣ ፫ አመነምሃት ግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1859 እስከ 1832 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአባቱ 3 ሰኑስረት ተከታይ ነበር።

በኻኻውሬ 3 ሰኑስረት ዘመነ መንግሥት በ1879 ዓክልበ. ግድም ልጁን ፫ አመነምሃት ከእርሱ ጋር በጋርዮሽ ወደ ዙፋኑ አስነሣው። ስለዚህ የ፫ አመነምሃት ዘመን መጀመርያ ዓመት የሚቆጠር ከ1879 ዓክልበ. ግድም ይሆናል። በጠቅላላ ለ47 ዓመታት ያህል እንደ ገዛ ይታወቃል።

የ፫ አመነምሃት ሐውልት

አንድ ሀረም «ጥቁሩ ሀረም» ጀምሮ ነበር ግን አሠራሩ ተቸግሮ አልጨረሰውም፤ ሌላ ታላቅ ሀረም ጀመረ። በአባይ አሮንቃ አንድ ቦይ ከመቆፈሩ የተነሣ ሞኤሪስ ሐይቅ ተፈጠረ።

በ1850 ዓክልበ. ግድም ዋና ሚኒስትሩ ቀቲ ነበረ። «የራይንድ ስነ ቁጥር ፓፒሩስ» የተባለው ጽሑፍ በኒመዓትሬ ዘመን ነበር የተቀነባበረው።

ማኔጦን በኋላ ዘመን በግሪክኛ ሲጽፍ አመነመስ ይለዋል። በመጨረሻው ዓመት ልጁን 4 አመነምሃት የጋርዮሽ ፈርዖን አደረገው።

ቀዳሚው
3 ሰኑስረት
ግብፅ ፈርዖን
1859 (1879)-1832 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
4 አመነምሃት