ከ«የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፪» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
Added links
Tags: በንፋስ ስልክ Mobile app edit iOS app edit
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit

መስመር፡ 4፦ መስመር፡ 4፦
|image=[[ስዕል:ፀሎተ ሐሙስ.jpeg]]
|image=[[ስዕል:ፀሎተ ሐሙስ.jpeg]]
[[File:Livre.png|88px]]

[[File:Livre.png|88px]]

ዘቅዱስ ሕርያቆስ
|data1=ዘቅዱስ ሕርያቆስ

፸፯ ፤ እንዲህም እናምናለን እንዲህም እንታመናለን የሃይማኖትም ጸሎት እንበል ።

፸፯ ፤ እንዲህም እናምናለን እንዲህም እንታመናለን የሃይማኖትም ጸሎት እንበል ።

በ07:05, 12 ኦክቶበር 2021 የታተመው ያሁኑኑ እትም

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፪

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

፸፯ ፤ እንዲህም እናምናለን እንዲህም እንታመናለን የሃይማኖትም ጸሎት እንበል ።
፸፰ ፤ ጸሎተ ሃይማኖት (የሃይማኖት ጸሎት) በል ።
፸፱ ፤ ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ ። ቅድስት ድንግልንም ለሁሉድንቅ የሚሆን የፅንሷን ነገር እንዲህ እያልን እንመርምራት ድንግል ሆይ እሳተ መለኮት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ፊቱ እሳት ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው እንደምን አላቃጠለሽም ? ።
፹ ፤ ሰባት የእሳት ነበልባል መጋረጃ በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘጋጀ ወዴትስ ተጋረደ ከጎንሽ በቀኝ ነውን ወይስ ከጎንሽ በግራ ነውን ትንሽ አካል ስትሆኚ ? ።
፹፩ ፤ የሚያንፀባርቅ ነደ እሳት የሚከበው ኪሩቤል የተሸከሙትን ዙፋን በሆድሽ ውስጥ በወዴት ተዘጋጀ ወዴትስ ተተከለ ታናሽ ሙሽራ ስትሆኚ ? ።
፹፪ ፤ ከአገልጋይነት ጋራ እናትነት እንደምን ያለ ነው ። ከስፋት ጋራ የሆድ መጥበብ እንደ ንብ ያለ ሩካቤ ከቃል ድምፅ የተገኘ ፅንስ ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሐሊብ ።
፹፫ ፤ ይህንንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ የልጅሽን የባሕሩን ጥልቅነት ሊዋኝ ይወዳል የወዳጅሽ የመሠወሪያው ማዕበልም ያማታዋል ።
፹፬ ፤ ዳግመኛም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ ተሠውሮ ወደላይ ወጥቶ የሕያው መሠወሪያ የሆነውን ሊገልጥ ይወዳል ። ከነደ እሳትነቱ የተነሣ ይፈራል ከዐየራት ከእርቧቸው እርቦ አይደርስም ።
፹፭ ፤ ይህንንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ በነፋስ ትከሻ ተጭኖ በምሥራቅና በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ በዳርቻዎችም ሁሉ ሊበር ይወዳል ። የፍጡራንን አኗኗር ያይ ዘንድ የአብርሕትንም ጥልቅነታቸውን ይለካ ዘንድ የሰማይን ርዝመቱን ያውቅ ዘንድ በሁሉ ዘንድ በሁሉም ይዞራል ። አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል ።
፹፮ ፤ አሁንም ገናናነቱን እንመርምር ጥልቅነቱንም እንጠናቀቅ ። የገናናነቱንም መጠን ለማመስገን የነብያትና የሐዋርያት አንደበት የማይቻለው ነው ።
፹፯ ፤ የማይደፈር ግሩም ነው ። በኛ ዘንድ ግን ትሑት ነው ። የማይገኝ ልዑል ነው ። በኛ ዘንድ ግን አርአያ ግብርን ነሣ ። የማይዳሰስ እሳት ነው ። እኛ ግን አየነው ዳሰስነውም ከእርሱም ጋራ በላን ጠጣን ። አሁንም እንዲህ እያልን እናመስግነው ።
፹፰ ፤ ቅዱስ እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው ።
፹፱ ፤ ድንግል ሆይ የሚበላውን ያፈራሽልን የሚጠጣውን ያስገኘሽልን ።
፺ ፤ ወዮ ካንቺ የተገኘ ኅብስት በማመን ከርሱ የሚቀበሉ ሕይወትንና ደኅንነት የሚሰጥ ነው ።
፺፩ ፤ ወዮ ካንቺ የተገኘ ኅብስት በማመን ከርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች የማይላመጥ ጽኑ ነው ። ይኸውም ኃያል የሚሆን የአድማስ ድንጋይ ነው ።