Jump to content

ሞልዶቭኛ

ከውክፔዲያ

ሞልዶቭኛ (limba moldovenească ሞልዶቨኛስክዕ) በሞልዶቫ ሬፑብሊክና በትራንስኒስትሪያ የሚናገር የሮማንኛ አይነት ነው። በሞልዶቫ ሕገ መንግሥት መሰረት ሞልዶቭኛ የአገሪቱ መደበኛ ቋንቋ ሲሆን አብዛኞቹ የቋንቋ ምሁሮች ግን ከይፋዊ ሮማንኛና ከይፋዊ ሞልዶቭኛ መካከል ምንም ልዩነት የለም ባዮች ናቸው።

ሞልዶቭኛ ማለት ደግሞ የሞልዶቫና የስሜን ሮማንያ ቀበሌኛ ሊሆን ይችላል።

ሞልዶቭኛ የሚጻፍበት ፊደል ወይም በላቲን አልፋቤት ወይም በቂርሎስ አልፋቤት ሊሆን ይችላል። አሁኑኑ የላቲን አልፋቤት በሞልዶቫ ሬፑብሊክ ይፋዊ ሲሆን በትራንስኒስትሪያ ግን የቂርሎስ አልፋቤት ይፋዊ ነው። ቅድም ሲል የሶቭየት ኅብረት ክፍላገር ስትሆን እስከ 1989 እ.ኤ.አ. ድረስ የቂርሎስ አልፋቤት በሞልዳቪያን ሶቭየት ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ውስጥ የቂርሎስ ጽሕፈት ይፋዊ ነበር።

ሞልዶቭኛ ከሮማንኛ የተለየ ቋንቋ መሆኑ በጣም የሚያከራከር ጉዳይ ነው። ሆኖም የሞልዶቫ ሕገ መንግሥት ይፋዊ ከማድረጉ በላይ በትራንስኒስትሪያ ከሩስኛዩክሬንኛ ጋራ መደበኛነት አለው። የትራንስኒስትሪያ ነጻነት ግን ከሌሎች አገራት ገና አልተቀበለም።

የሞልዶቫ ሳይንስ ተቋም ቋንቋውን ቢያስተዳድርም 'ሮማንኛ' ይለዋል። የሮማኒያ መካነ ጥናት ደግሞ ለሮማንያ ቋንቋ ሲያስተዳድር አንዳንድ ከ1989 በኋላ ያደረገው የአጻጻፍ ለውጥ በሞልዶቫ ውስጥ አልተቀበለም። ስለዚህ ከሁለቱ ይፋዊ ቋንቋዎች መካከል ጥቃቅን የአጻጻፍ ለውጥ ይኖራል። ከዚህ አጠገብ ከሁለቱ አገሮች መነጋገርያዎች መካከል ሌሎች ትንንሽ ለውጦች አሉ።