ሥነ ኑባሬ
Appearance
ሥነ ኑባሬ ማለት ስለ "ህላዌ" የሚያጠና የጥናት ዘርፍ ናቸው፤ በሥነ-ኑባሬ ሁለት ነጥቦች አሉ፤ አንዱ አካል ማለትም "ማንነት" ሲሆን ሁለተኛው ህላዌ ማለትም "ምንነት" ነው፤ አካል የህላዌ መገለጫ ሲሆን ህላዌ የአካል መሰረት ነው። ሌላው በሥነ-ኑባሬ ጥናት ውስጥ ሦስት አማራጮች አሉ፤ አንዱ "ነው" ሁለተኛው "አይደለም" ሦስተኛው "የእርሱ ነው" ናቸው፤ ለምሳሌ የፈጣሪ ንግግር ፈጣሪም አይደለም፣ ፍጡርም አይደለም፤ ግን የፈጣሪ ባህርይ ነው፤ ልክ የእኔ ንግግር እኔ ሳልሆን ከእኔም ውጪ ሳይሆን የእኔ ባህርይ ነው።
ይሁንና በአንዳንድ ፈላስፋዎች ዘንድ የኑባሬ ትርጉም ከላይ ከተሰጠው የጠበበ ሆኖ ይገኛል። ኑባሬ ማለት የክስተቶች ተሸካሚ ሆኖ ነገር ግን ክስተቶችን አይጠቀልልም። ለምሳሌ አንድ ሎሚ፣ ቀለሙ፣ ድብሉቡልነቱ፣ ሽታው፣ ወዘተ... የሎሚው ክስተት ሲሆኑ፣ ነገር ግን እነዚህም ባሕርዮች ሁሉ ተሸክሞ የሚገኘው ፣ መኖሩ ወይንም ኑባሬው ይባላል። ስለዚህ ኑባሬው የሎሚው ዲበ አካላዊ ባሕርዮት ሆኖ ይገለጻል ማለት ነው።