ቃረህ ኻዎሰሬ
Appearance
==
ቃረህ ኻዎሰሬ | |
---|---|
የቃረህ ስም በጢንዚዛ ዕንቁ ላይ እንደ ተጻፈ | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1801-1791 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ያዓሙ ኑብዎሰሬ |
ተከታይ | አሙ አሆተፕሬ |
ሥርወ-መንግሥት | 14ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ቃረህ ኻዎሰሬ ግብጽን በ፪ኛው ጨለማ ዘመን (14ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1801 እስከ 1791 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት ከሥነ ቅርስ እንደሚያስረዳው፣ ከያዓሙ ቀጥሎ ቃረህ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለጤቤስ ፈርዖኖች ተገዥ ሆኖ ነገሠ። ሕዝቡ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ።
አያሌ (30 ያህል) የ«ቃረህ» ወይም የ«ኻዎሰሬ» ጢንዚዞች በዚያ ወቅት በዙሪያው እንደ ገዛ ይገልጻሉ፤ እነዚህም ስያሜዎች አብረው ባይታዩም ለአንዱ ፈርዖን መሆናቸው ይታስባል። ከነዚህ ቅርሶች አንዱ የጢንዚዛ ዕንቁ በኢያሪኮ በከነዓን ተገኝቷል።[1] ሆኖም በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ ቃረህ በኋላ በ15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ወይም በ16ኛው ሥርወ መንግሥት ውስጥ ነበር የነገሠ።
ቀዳሚው (ያዓሙ ኑብዎሰሬ) |
የአባይ ወንዝ አፍ (ጌሤም) ፈርዖን | ተከታይ አሙ አሆተፕሬ |
- ^ Kim Ryholt, 1997, The Political Situation in Egypt During the Second Intermediate Period p. 199