ባንግኮክ
Appearance
(ከባንኮክ የተዛወረ)
ባንግኮክ (ጣይኛ፦ กรุงเทพฯ /ክሩንግ ጠፕ/) የታይላንድ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 6,320,174 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 13°44′ ሰሜን ኬክሮስ እና 100°30′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ባንግኮክ ከ1400 ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ መንደር ሆኖ «ጦንቡሪ» ተብሎ ይታወቃል። ይህ በ1769 ዓ.ም. የጦንቡሪ መንግሥት ዋና ከተማ ሆነ። በ1774 ዓ.ም. ስሙ ከጦንቡሪ ወደ ክሩንግ ጠፕ ተቀየረ፣ የአገሩም ስም ደግሞ «የራታናኮሲን መንግሥት» ሆነ። «ክሩንግ ጠፕ» እስካሁን ይፋዊ ስሙ ሆኗል፤ «ባንግኮክ» የሚለው ስያሜ እንዲያውም መጠሪያ ሲሆን በተለይ የውጭ አገር ሰዎች እንዲህ ይሉታል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |