Jump to content

ቤይሩት

ከውክፔዲያ

ቤይሩት (بيروت) የሊባኖስ ዋና ከተማ ነው።

ቤይሩት

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 1,916,100 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,171,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 33°52′ ሰሜን ኬክሮስ እና 35°30′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

እጅግ ጥንታዊ የፊንቄ ከተማ ('በሩት') ነበር። ከክ. በ. በ14ኛ ክፍለ ዘመን በ'አማርና ደብዳቤዎች' መዝገብ ውስጥ ስሙ መጀመርያ ይገኛል። የ'ቢሩታ' ንጉስ አሙኒራ 3 ደብዳቤዎች ለግብጽ ፈርዖን ጽፎ ነበር። በ148 ክ.በ. የመቄዶን አዛዦች ለሴሌውቅያ ዙፋን ሲታገሉ ከተማው ጠፍቶ፣ በቶሎ እንደገና ተሠርቶ ስሙ ሎዶቅያ በፊንቄ ተባለ። ሮማውያንም ከ1ኛ ክፍለ ዘመን ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ ስሙን ኮሎኒአ ዩሊያ አውግስጣ ፌሊክስ ቤሪውቱስ አሉት።