ታሽሉልቱም የታላቁ ሳርጎን ሚስት ነበረች። ስሟ ከሥነ ቅርስ የሚታወቅ ከአንድ የአልባስጥሮስ ገል ብቻ ነው፤ ሎሌዋ ለመቅደስ ያቀረበ ዕቃ መሆኑ በጽሑፉ ይነብባል።[1] ምናልባት የአካድ ንግሥት እንደሆነችና የሳርጎንን ልጆች ሪሙሽ፣ ማኒሽቱሹ፣ ኤንሄዱአና፣ ሹ-ኤንሊል እና ኢላባ-ኢስታካል እንደ ወለደች ይገመታል።