Jump to content

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

ከውክፔዲያ

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 18 ቀን 1973 ዓ.ም ተወለደ፡፡ ኃይሌ የረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ሯጭ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የተዋጣለት ነጋዴ ባለሀብት ነው፡፡ ኃይሌ ሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች ተሳትፎ በ10,000 ሜትር ሩጫ ሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን እና አራት የዓለም ሻምፒዮናዎችን አሸንፏል። ኃይሌ በበርሊን ማራቶን አራት ጊዜ በተከታታይ ያሸነፈ ሲሆን፤ በዱባይ ማራቶንም ሶስት ተከታታይ ድሎችን አስመዝግቧል። በቤት ውስጥም አራት የአለም ዋንጫዎችን አግኝቶ የ2001 የአለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮን ሆኗል።

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከ1,500 ሜትር ርቀት እስከ ማራቶን ድረስ ባሉት ርቀቶች ተወዳድሯል፡፡ በዚህም መሰረት በቤት ውስጥ፣ በጎዳና ላይ እና በአገር አቋራጭ ሩጫዎች ተወዳድሮ አሸንፏል። ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን 61 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሪከርዶችን በመስበር 27 የአለም ሪከርዶችን አስመዝግቧል፡፡ በዚህም ድሉ በታሪክ መዝገብ ላይ ከታላላቅ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዱ ነው ተብሎ ተመዝግቧል።

ኃይሌ በ2008 ዓ.ም በበርሊን በተደረገው የማራቶን ውድድር በ2:03:59 ሰዓት በመግባት የራሱን ክብረ ወሰን በ27 ሰኮንዶች በማሻሻል ጭምር አሸንፏል፡፡ ይህ ክብረ ወሰን ለሦስት ዓመታት ያህል ሳይሻሻል ቆይቷል። ኃይሌ እ.ኤ.አ. ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በ10,000 ሜትር በአዋቂዎች የዕድሜ ምድብ የዓለም ክብረ ወሰንን እስካሁን እንደያዘ ነው፡፡

በትራክ እና በጎዳና ሩጫ ውድድር ባደረጋቸው የተለያዩ ድሎች ምክንያት ብዙዎች “የረጅም ርቀት ሩጫ ንጉሥ” ብለው ይጠሩታል። ኃይሌ እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም በኒው አፍሪካን ከ100 ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆኖ ተጠቅሷል።

እ.ኤ.አ. በ2020 ዓ.ም ታዋቂው የኦሮሞ ዘፋኝ ሃጫሉ ሁንዴሳ በሞተበት ወቅት በተፈጠረው ግርግር ወቅት የኦሮሞ ተወላጆች ቁጣቸውን የገለጡት ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች የንግድ ድርጅቶች እና ንብረቶች ላይ ነበር። በዚህም ግርግር የኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ተቃጥለዋል፡፡ 400 ሰራተኞችም ስራ አጥተዋል።