ናኮር
Appearance
1 ናኮር (ዕብራይስጥ፦ נָחֹור /ናሖር/) በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት የሴሮሕ ልጅና የታራ አባት ነበረ። (ሌላ 2 ናኮር ደግሞ የታራ ልጅና የአብርሃም ወንድም ነበር።)
ዘፍጥረት 11፡24-25 ስለ 1 ናኮር በአማርኛ እንደሚለው፣ የናኮር ዕድሜ 109 ዓመት ሲሆን ታራን ወለደ፣ ከዚያም ሴሮሕ 129 ዓመት ኖረ። በሌሎቹ ጥንታዊ ትርጉሞች ግን ቁጥሮቹ ይለያያሉ። በእብራይስጥ ትርጉም በ29 ዓመት ታራን ወለደ፣ ከዚያም 119 ዓመት ኖረ፤ በሳምራዊውም በ79 ዓመት ታራን ወለደ፣ ከዚያም 69 ዓመት ኖረ። በግሪክም በ79 ዓመት ታራን ወለደ፣ ከዚያም 129 ዓመት ኖረ።
በመጽሐፈ ኩፋሌ 10፡26-28 ዘንድ፣ ናኮር ከአባቱ ሴሮሕና ከእናቱ ሜልካ በ1744 አመተ አለም ተወለደ። የከላውዴዎን ዑር በተባለ ከተማ አድጎ አባቱ ሟርትን አስተማረው። በ1800 አ.አ. ናኮር ሚስቱን ኢዮስካን አገባት፤ እርሷም የከለዳዊው ኔስቴግ ልጅ ትባላለች። በ1806 አ.አ. ኢዮስካ ልጁን ታራን ወለደችለት፤ ስለዚህ እድሜው 62 ዓመታት ነበረ።