Jump to content

አንቅቲፊ

ከውክፔዲያ
የአሣ አጥማጅ ትርዒት፥ ከአንቅቲፊ መቃብር

አንቅቲፊ በደቡብ (ላይኛ) ግብጽ1ኛው ጨለማ ዘመንነቀን (3ኛው) እና የበህደት (2ኛው) ኖሞች ገዢ ነበረ። በዚያው ዘመን ከጤቤስ የራቁት ክፍሎች ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ስሜን ከጤቤስ ፈርዖኖች (11ኛው ሥርወ መንግሥት) ያመጹ ነበር። ስለዚህ አንቅቲፊ የጤቤስ መንግሥት ተጋጣሚ እና የ«ቀቲዎች» ወገን (በ10ኛው ሥርወ መንግሥት በስሜን ግብጽ የገዙ) ደጋፊ ነበር። ይህ ምናልባት በጤቤስ ፈርዖን 1 አንተፍ ዘመን ይሆናል።

የአንቅቲፊ ሕይወት ታሪክ በመቃብሩ ግድግዳዎች ስለ ተቀረጸ ይታወቃል። 1ኛው ኖም ከ2ኛውና 3ኛው ኖሞች ጋር በጤቤስ (4ኛው ኖም) ላይ እንደ ተባበሩ ይገልጻል። ሥራዊቱ ወደ ጤቤስ ዙሪያ ሄዶ የጤቤስ ሰዎች ፈርተው ከከተማቸው ለመውጣት አልደፈሩም በማለት ይመካል።

የረሃብ ዘመን ሲሆን አንቅቲፊ ደቡብ ግብጽን በገብስ ይመግብ ነበር። ከዚህ በላይ ገብሱን ወደ ስሜንና ወደ ደቡብ ልኮ በንግድ ለመዋቢያ ዘይት ወይም ሌላ ሸቀጣሸቀጥ ይለዋወጥ ነበር። እንዲህ ስላደረገ፥ አንቅቲፊ ለራሱ የነበረው አስተያየት ታላቅ ነበር። «እኔ ወደር የለሽ ጀግና ነኝ... ወደ ፊት የሚመጡ ትውልዳት በ1 ሚሊዮን ዓመታት ውስጥ የእኔን ሥራዎች መወዳደር አይቻላቸውም!» በመቃብሩ ጽሑፍ ብሏል።