አጃክስ (ፕሮግራም)
Asynchronous JavaScript እና XML
ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው - መጋቢት ፩፱፱፩
የፋይል ስም ቅጥያ - .js
የፋይል ቅርጽ - JavaScript
መነሻ ሃሳብ - ከJavaScript እና XML
አጃክስ (እንዲሁም AJAX /አጃክስ/ ፤ አጭር ለ “ Asynchronous JavaScript እና XML ” ወይም “ Asynchronous JavaScript transfer ( x -fer)” ) የድረ-ገጽ መገንቢያ ስልቶች ቅንጅት ሲሆን የተለያዩ የድረ-ገፅ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በተመሳሳይ ጊዜ የማይዋቀሩ (ኤሲንክሮነስ) የድረ-ገጽ መተግበሪያዎችን (ዌብ አፕሊኬሽኖችን) የሚያቀናጅ ነው። በአጃክስ፣ ዌብ አፕሊኬሽኖች ጥቅም ላይ እየዋለ ያለውን ነባሩን ገጽ እና ባህሪውን ሳያዛቡ ከበስተጀርባ ዳታን ከሰርቨር መላክ እና መቀበል ያስችላሉ ። የዳታ መለዋወጫ እና የአቀራረብ እርከኖችን በመለየት፣ አጃክስ ድረ-ገጾችን እና፣ በተዘዋዋሪ፣ የድር መተግበሪያዎች፣ አጠቃላይ ገጹን እንደገና መጫን ሳያስፈልግ ይዘታቸውን እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል። በተግባር፣ ዘመናዊ ትግበራዎች ከXML ይልቅ JSONን ይጠቀማሉ።
አጃክስ ቴክኖሎጂ ሳይሆን የፕሮግራሚንግ ጽንሰ-ሀሳብ ነው። HTML እና CSSን በማጣመር መረጃን ቅርጽ የማስያዝ እና የማስዋብ ስራን መስራት ይቻላል። ድረ-ገጽን JavaScript በመጠቀም ማስተካከል እንዲሁም በቅልጥፍና ማሳየት የሚቻል ሲሆን ይህም ደግሞ ተጠቃሚው ከአዲሱ መረጃ ጋር መስተጋብር እንዲፈጥር ያስችለዋል። በሲስተሙ ውስጥ በነባር የሚገኘው XMLHttpRequest አጃክስን በድረ-ገጾች ላይ ለማስፈጸም ይጠቅማል፣ ይህም ድረ-ገጾች ገጹን ሳያድሱ ይዘትን ወደ ስክሪኑ እንዲያሳልፉ ያስችላቸዋል። አጃክስ አዲስ ቴክኖሎጂ አይደለም ወይም አዲስ ቋንቋም አይደለም። ይልቁንም በአዲስ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ነባር ቴክኖሎጂ ነው።
አጃክስ[1] የሚለው ቃል አሁን አሁን ከበስተጀርባ ካለው ሰርቨር ጋር የሚገናኙ እና የገጹ ሁኔታ ውስጥ ጣልቃ የማይገቡ የድረ-ገጽ አፕሊኬሽኖችን ለመተግበር የሚያገለግሉ ሰፊ የዌብ ቴክኖሎጂዎች መዋቅርን ይወክላል። ጄሲ ጀምስ ጋሬት አጃክስ የሚለውን ቃል ባወጣው መጣጥፍ ውስጥ የሚከተሉት ቴክኖሎጂዎች እንደተካተቱ ገልጿል።
- HTML (ውይም XHTML) እና CSS ለአቀራረብ
- Document Object Model (DOM) ለተለዋዋጭ ማሳያ እና ከዳታ ጋር ለመስተጋብር
- JSON ውይም XML ለዳታ ልውውጥ፣ እና XSLT ለXML ማስትካከያ
- XMLHttpRequest ለኤሲንክሮነስ ንግግር
- JavaScript እነዚህን ቴክኖሎጂዎች አንድ ላይ ለማምጣት
- ^ Jesse James Garrett (18 February 2005). "Ajax: A New Approach to Web Applications". AdaptivePath.com. Archived from the original on 10 September 2015. በ24 July 2024 የተወሰደ.