Jump to content

ኡማ

ከውክፔዲያ
ኡማ
(ተል ጆኃ)
ሥፍራ
ኡማ is located in መስጴጦምያ
{{{alt}}}
መንግሥት ኡሩክ፣ ኪሽ፣ አዳብ፣ ኡማ፣ አካድ፣ ዑር፣ ኢሲን፣ ላርሳ ወዘተ.
ዘመን 2375-1777 ዓክልበ. ግድም
ዘመናዊ አገር ኢራቅ
ጥንታዊ አገር ሱመር

ኡማሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ጆኃ ተብሎ በዘመናዊው አገር ኢራቅ ውስጥ ይገኛል።

ኢናና ወደ ታቸናው አለም ስትወርድ በተባለ ሱመራዊው ትውፊት ሰነድ መሠረት፣ አጋንንት የኡማ ድሃ አለቃ ሻራን ወደ ሢኦል ለመውሰድ ሲያስቡ፣ ኢናና እንዳይይዙት ታሳምናቸዋለች። በሻራ ፈንታ አጋንንቱ በቅንጦት የኖረውን የኡሩክን ንጉስ ዱሙዚድን ይወስዳሉ።

ለረጅም ዘመን የኡማ ዋና ተወዳዳሪ ከተማ ላጋሽ ነበረ። የኡማ ንጉስ ሉጋል-ዛገሲ (2102-2077 ዓክልበ. ግድም) በተለይ ሰፊ ግዛትና የሱመር ላዕላይነት አገኘ። በኋላ በኡር መንግሥት ዘመን ትልቅ ከተማ ነበር። በ1777 ዓክልበ. የላርሳ ንጉሥ ሱሙኤል ኡማን አጠፋው። በፍርስራሹ ላይ ብዙ ቅርሶች ቢገኙም ከ1995 ዓ.ም. ጦርነት ጀምሮ ሌቦች በዝተው በመስረቃቸው ለቦታው ጉዳት ሁነዋል።