Jump to content

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፭

ከውክፔዲያ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፭

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፻፲ ፤ አቤቱ ሞትህን ቅድስ ትሣኤህንም እንናገራለን ። ዕርገትህን ዳግመኛ መምጣትህን እናምናለን። ጌታችን አምላካችን ሆይ እንለምንሃለን ። እንማልድሃለን ።
፻፲፩ ፤ አቤቱ እንደዚያን ጊዜ ይህን ኅብስት (እማሬ) ባርከህ ቆርሰህ ስጥ (አንድ ጊዜ ኅብስቱን ይባርክ)
አሜን ።
፻፲፪ ፤ አቤቱ እንደዚያን ጊዜ ይህን ጽዋ (እማሬ) ባርከህ አክብረህ ስጥ (አንድ ጊዜ ጽዋውን ይባርክ) ። ዳግመኛም አንድ ጊዜ በሁለቱም ላይ ይባርክ ።
አሜን ።
፻፲፫ ፤ ይህንንም የኔን ማገልገል (ክህነት) አንጻ ምረጥ ውደድም ።
አሜን ።
፻፲፬ ፤ በዚህ ምሥጢር እየተራዳኝ ከኔ ጋር ያለ ይህንን ካህን እርሱንም እኔንም ሥጋህን እንደ ገነዙት እንደ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ አድርገን ።
አሜን ።
፻፲፭ ፤ እንደ አገልጋይ ሥርዐት የሚያገለግል ይህንንም ዲያቆን ዳግመኛ ወደሚበልጥ ወደ እኛ ክህነት ሹመት ማዕረግ አድርሰው ጸጋንና ጽድቅን ባለሟልነትንም የተመላ አድርገው የሥላሴን አኗኗር በልዕልና አይቶ በመንፈስ ቅዱስ መውረድ ፈፅሞ እንዳደነቀ እንደ እስጢፋኖስ አድርገው ።
አሜን ።
፻፲፮ ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡትን ሕዝብህንም ከካህናቱና ከዲያቆናቱ ጋራ ከታናሹም ከታላቁም ጋራ ቅዱስ ምሥጢርህን ለመቀበል አብቃ ይቅር በል እንጂ አትፍረድ አሜን አቤቱ ማረን አቤቱ ራራልን አቤቱ ይቅር በለን ።
፻፲፯ ፤ አቤቱ ክርስቶስ ማረን ፫ ጊዜ ።
፻፲፰ ፤ በፍፁም ልብ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንለምነው ያማረ የመንፈስ ቅዱስ አንድነትን ይሰጠን ዘንድ ።
፻፲፱ ፤ በፊት እንደነበረ ለዘላለሙ ለልጅ ልጅ ይኖራል ።
፻፳ ፤ (በዚህ ጊዜ በጣቱ ጠምቆ በደሙ ስጋውን ይቅባ) ከርሱ ለሚቀበሉ ሰዎች ሁሉ ለዘላለም ሕይወት ይሆናቸው ዘንድ አንድ አድርገህ ስጣቸው ።
፻፳፩ ፤ የአንተ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ መሆንን ስጠን ። በዚህም ጵርስፎራ (በሥጋ በደሙ) አድነን ለዓለሙ ሁሉ በምትሆን በአንተ ለዘላለሙ ሕያዋን እንሆን ዘንድ ።
፻፳፪ ፤ የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው የጌትነቱም ስም ይመስገን ። ይሁን ። ይሁን ። የተመሰገነ ይሁን ።
፻፳፫ ፤ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ላክልን ።