የሜዳ ቀይ ሕንዳውያን እጅ ምልክት ቋንቋ
Appearance
የሜዳ ቀይ ሕንዳውያን እጅ ምልክት ቋንቋ (Plains Indian Sign Language ወይም PISL) በዩናይትድ ስቴትስ ታላቅ ሜዳዎች ላይ በኖሩት በስሜን አሜሪካ ኗሪዎች (ቀይ ሕንዳውያን) የተፈጠረ የእጅ መነጋገሪያ ነበረ።
በአሜሪካና በካናዳ በሮኪ ተራሮች ምሥራቅና በሚሲሲፒ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው አገር በብዛት ሰፊ ሜዳዎች ነው። በነዚህ ላይ ብዙ የተለያዩ የአገር ኗሪ ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ጎሽን እያደኑ ይመላለሱ ነበር። እነዚህም አገሮች ሁሉ የየራሳቸው ቋንቋ ነበራቸው። ከዚህ በላይ ልሳናታቸው ባልተዛመዱ ቤተሠቦች ውስጥ ስለሆነ እርስ በርስ በመነጋገር ትንሽ ተቸገሩ። በዚህ ምክንያት ጎሣዎቹ ሁሉ የሚጠቀሙበት የእጅ መነጋገሪያ ቋንቋ ተለማና ተስፋፋ።
ይህ ዘይቤ በአውሮፓውያን መጀመርያ በ1533 ዓ.ም. በስፓንያዊው አለቃ ኮሮናዶ ታየ። በ1877 ዓ.ም.፣ ቋንቋውን የቻሉት ኗሪዎች ቁጥር በ110፣000 ተገመተ። እነዚህ ከአልጎንኲን ቤተሠብ የሲክሲካ (ብላክፉት)፣ የጺጺስታ (ሻየን)፣ የሂኖኖኧይኖ (አራፓሆ) ተነጋሪዎች፣ እንዲሁም የካወጉ (ካዮዋ) እና የላኮታ (ሱ) ተነጋሪዎች ይጠቀልል ነበር።[1] ነገር ግን በ1960ዎቹ 'ከዚህ ቁጥር በጣም ጥቂት ከመቶ' ቀሩ።[1] ዛሬም ጥቂት PISL የሚችሉ አሉ።
PISL ልዩ ስዋሰው አለው።
- አንተ የሕንዳውያን ምልክት ቋንቋ ትችላለህ?
- (ምልክቶች፦) <ጥያቄ> - <አንተ> - <ማወቅ> - <ቀይ ሕንዳዊ> - <ምልክት ቋንቋ> - <መናገር>
- ^ ሀ ለ Tomkins, William: Indian sign language. [Republication of "Universal Indian Sign Language of the Plains Indians of North America" 5th ed. 1931]. New York : Dover Publications 1969. (p. 7)
- Newell, Leonard E. (1981). A stratificational description of Plains Indian Sign Language. Forum Linguisticum 5: 189-212.
- "PISL"
- Ethnologue report for language code:psd
- "Indian" Sign Language Dictionary መዝገበ ቃላትና ብዙ መራጃ (እንግሊዝኛ)
- "Sign Language Among North American Indians Compared With That Among Other Peoples And Deaf-Mutes," First Annual Report of the Bureau of Ethnology to the Secretary of the Smithsonian Institution, 1879-1880, Government Printing Office, Washington, 1881, pages 263-552
- በ1930ዎቹ የተቀረጸ የሕንዳውያን ምልክት ቋንቋ መግለጫ ቪዲዮ፣ በዩቱብ
- "The Indian Sign Language" 1885 by William Philo Clark on Google Books