Jump to content

የቾላ ሥርወ መንግሥት

ከውክፔዲያ
ቾላዎች ያሠሩ አንድ ቤተ መቅደስ

የቾላ ሥርወ መንግሥት በደቡባዊ ሕንድ አገርና በኋላም በስሪ ላንካ ቢያንስ ከ300 ዓክልበ ጀምሮ እስከ 1271 ዓም የቆየ የታሚል ብሔር መንግሥት ነበረ። በሥነ ሕንጻ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በመርከብ ኃይልም ለሥልጣኔ አንጋፋዎች ሆኑ።

ከታሪካዊ መዝገቦች እስከምናውቅ ድረስ ቢያንስ ከ300 ዓክልበ. ጀምሮ ተገኙ ሲባል፣ እንደ ልማዳዊ ታሪካቸው በጥንታዊ ታሚልኛ ሥነ ጽሑፍ ከዚያ በፊት ብዙ አፈ ታሪካዊ ነገሥታት ይጠቀሳሉ። ነገር ግን ለነዚህ ቅድመ-ታሪካዊ ነገሥታት፣ ማንኛውም ቅድመ-ተከተል ወይም ዘመናት መረዳት ያስቸግራል። በአንድ ግመት፣ መጀመርያው ቾላ ንጉሥ «ኤሪ ኦሊያን ቫኤንድሂ» የነገሠው ከ3028 ዓክልበ. ጀምሮ ቢሆን፣ ይህ ቁጥር ግን አጠያያቂ ነው። አንዱ አፈ ታሪካዊ የቾላ ንጉሥ ካንታማንአጋስትያ (ከርግ ቬዳ ደራሲዎች አንዱ) ዘመን እንደ ኖረ ሲባል፣ ይህ ምናልባት 1200 ዓክልበ. አካባቢ ያደርገዋል፤ አጋስትያም ደግሞ በታሚሎች ትውፊት መሠረት ታሚሎቹን ከስሜን ወደ ደቡብ ሕንድ የመራቸው ቅዱስ ቄስ ነበረ።

በታሪካዊ ዘመን ደግሞ ለረጅም ዘመን ስለ ታወቁ ብዙ ሥነ ጥበብና ኪነት ትተዋል።