Jump to content

ዮፍታሄ ንጉሤ

ከውክፔዲያ
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ

ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ[1]) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም።

የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል። ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ [[ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸው ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል።[2]

የድርሰት ሥራዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ መዝገበ ህትመት ዳሰሳ፣ ገጽ 13
  2. ^ ‘ሪፖርተር’ Ethiopian Reporter, “የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ” 09 SEPTEMBER 2012