ጃካርታ
Appearance
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 13,194,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 8,389,443 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 06°08′ ደቡብ ኬክሮስ እና 106°45′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ከ389 እስከ 1519 ዓ.ም. ድረስ ስሙ «ሱንዳ ከላፓ» ነበረ። ከዚያም በኋላ እስከ 1611 ዓ.ም. ድረስ ስሙ «ጃያካርታ» ተባለ። በ1611 ዓ.ም. የሆላንድ ሰዎች ስሙን ወደ «ባታቪያ» ቀየሩት፤ በ1941 ዓ.ም. ደግሞ ኢንዶኔዥያ ነጻነትዋን ስታገኝ ስሙ «ጃካርታ» ሆነ፤ የአገርም ዋን ከተማ በይፋ ተደረገ። ይህ ስም ከቀድሞው «ጃያካርታ» ሲሆን ትርጉሙ «ፍጹም ድል ማድረግ» ያህል ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |