ጥናት
ይህ መጣጥፍ የውክፔዲያ የአቀማመጥ ልምዶችን እንዲከተል መስተካከል ይፈልጋል። |
የውስጥ አርበኞች ገ ፀባህሪያት አቀራረብ በተመረጡ የአማርኛ ልቦለዶች በ ዘቢባ ነስሩ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ - ጽሁፍ ክፍል ለአርት ባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጽሁፍ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሰኔ 2001 ዓ . ም የውስጥ አርበኞች ገ ፀባህሪያት አቀራረብ በተመረጡ የአማርኛ ልቦለዶች በ ዘቢባ ነስሩ አማካሪ ቴዎድሮስ ገብሬ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ - ጽሁፍ ክ ፍል ለአርት ባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጽሁፍ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሰኔ 2001 ዓ . ም ምስጋና ከሁሉ አስቀድሞ እዚህ እንድደርስ ላደረገኝ አላህ(ሱ.ወ) ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ከልጅነት እስከ አሁን ድረስ እዚህ ደረጃ እንድደርስ ላደረጋችሁኝ ቤተሰቦቼ አላህ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ፡፡ ጀዛእ ኩሙላህ ኸይር ይህንን ጥናታዊ ጽሁፍ የአሁኑን መልኩን እንዲይዝ ረቂቁን በማረም በማስተካከልና ገ ንቢ አስተያየቶችን በመስጠት እገዛ ላደረጉልኝ አማካሪዬ አቶ ቴዎድሮስ ገብሬን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ I ማውጫ ምዕራፍ አንድ ገጽ ምስጋና መግቢያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1 1.1 የጥናቱ ዳ ራ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1 1.2 የጥናቱ አላማ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 1.3 የጥናቱ ዘዴ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 1.4 የጥናቱ ወሰን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 1.5 የጥናቱ አስፈላጊነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 1.6 የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 ምዕራፍ ሁለት 2. ክለሳ ድርሳ ናት 2.1 የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3 2.2 ንድፈ ሀሳባዊ ሥራ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5 2.2.1 የአርበኛ ምንነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5 ምዕራፍ ሦስት 3. የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪያት አቀራረብ በተመረጡ የአማርኛ ልቦለዶች 3.1 በረመጥ ል ቦለድ ውስጥ የሚገኙ የውሰጥ አርበኞች ገፀባህሪያት አቀራረብ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7 3.2 ለጣምራ ጦር ልቦለድ ውጥስ የሚገኙ የውስጥ አርበኞች ገፀባህሪያት አቀራረብ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .13 3.3 በየልምዣት ውስጥ የሚገኘው የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪ አቀራረብ . . . . 16 ምዕራፍ አራት ማጠቃለያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 18 ዋ ቢ ፅሁፎች II ምዕራፍ አንድ መግቢያ ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በረመጥና በጣምራ ጦር እና በየልምዣት ልቦለዶች ላይ የተሠራ ሲሆን ትኩረት የሚያደርገው በልቦለዱ ውስጥ ባሉ የውስጥ አርበኞች ገፀባህሪያት አቀራረብ ላይ ነው፡፡ ጥናታዊ ጽ ሁፍ አራት ምዕራፎች አሉት ምዕራፍ አ ንድ ላይ የጥናቱ ዳራ፣ የጥናቱ አላማ፣የጥናቱ ዘዴ፣ የጥናቱ ወሰን፣ የጥናቱ አስፈላጊነት እና የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት ተካተዋል፡፡ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ክለሳ ድርሳና ት ማለትም የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት ንድፈ ሀሳባዊ ዳ ራ አለ፡፡ በምዕራፍ ሦስት ለጥናቱ በተመረጡት ሦስት ልቦለዶች ትንተና ይሰጥባቸዋል፡፡ ትንተናው የሚከናወነው የገፀባህሪያቱን አቀራረብ በማጤን ይሆናል፡፡ ጥናቱ ለትንተና ው በቀረቡት መጸሐፍት (በረመጥ፣በጣምራ ጦር እና በየልምዣት) ውስጥ የምና ገኛቸውን የውስጥ አርበኞች ገፀባህሪያት አቀራረብ ይተነትናል፡፡ 1.1 የጥናቱ ዳራ ለጥናቱ የተመረጡት ልቦለዶች ረመጥ እና ጣምራ ጦር በ ጦርነት ታሪክ ላይ ተመሰርተው የተፃፉ ሲሆን የልምዣት ደግሞ የተመረጠበት ምክ ንያት በልቦለድ ታሪክ ላይ የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪ ስለሚገኝ ነው፡፡ ረመጥ ታሪካዊ ልቦለድ ሲሆን ፈጠራ ታክሎበት ታሪካዊ ልቦለድ ሆኗል፡፡ መጽሐፉ የተፃፈ በቀኝ አዝማች ታደሰ ዘወልዴ እና በገበየሁ አየለ ነው፡፡ የመጽሐፉ ታሪክ የሚያተኩረው በ1928ቱ የ ፋሽሲ ት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ላይ ነው፡፡ ጣምራ ጦር በገበየሁ አየለ የተፃፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ታሪኩ 1969 - 70 የነበረውን የኢትዮጵያን ና የሶማሊያን ጦርነት መሠረት አድርጐ የተፃፈ ልቦለድ ነው፡፡ የልምዣት በ1980 የታተመ በሀዲ ስ አለማየሁ የተ ፃፈ ልቦለድ ነው፡፡ 1 1.2 የጥናቱ አላማ የዚህ ጥናት አላማ በረመጥ ፣ በጣምራ ጦር እና በየልምዣት ውስጥ የሚገኝ የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪያት እንዴት እንደቀረቡ ማሳየት ነው፡፡ 1.3 የጥናቱ ዘዴ ይህን ጥናት ለማካሄድ በመጀመሪያ የውስጥ አርበ ኛ ገፀባህሪያት የሚገኙባቸው ሦስት መጻህፍት ተመረጡ፡፡ ከተለያዩ በገፀባህሪያት ጋር በተያያዘ የተደረጉ ጥናቶ ች ን ለማየት ተሞክሯል፡፡ ጥናቱ የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪያት እንዴት እንደቀረቡ መጽሀ ፎቹን በማንበብ የተሠራ ነው፡፡ 1.4 የጥናቱ ወሰ ን በዚህ ጥናት የተተነተኑት ልቦለዶች ሦስት ና ቸው፡፡ የገበየሁ አየለ ጣምራ ጦር /1978/ የቀኛዝማች ታደሰ ዘወልድ እና የገበየሁ አየለ ረመጥ /1983/ እና የሀዲስ አለማየሁ የልምዣት /1980/ ናቸው፡፡ 1.5 የጥናቱ አስፈላጊነት ይህ ጥናት በሦስቱ ልቦለዶች የ ውስጥ አርበኛ ገፀባህሪያት እንዴት እንደቀረቡ ከማሳየት ባ ሻገር ስለገፀባህሪያት አቀራረብ ለማጥናት ለሚፈልግ ሰው የመነሻ ሀሳብ የመስጠት ፋይዳ አለው፡፡ 1.6 የጥናቱ አነሳሽ ም ክንያት የልዩ ልዩ የገፀባህሪያት ዓይነቶችን አሳሳል ሁኔታ የሚያሳዩ ብዛት ያላቸው ጥናቶች ቢኖሩም አርበኛ ገፀባህሪያት አቀራረብ ሁኔታ የሚያዳስሱ ጥናቶ ች አልተገኙም፡፡ ይህ ሁኔታ የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪያት በልቦለድ ሥራዎች ውስጥ እንዴት ቀርበዋል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ መፈለግን አላማው ያደረገውን ይህን ጥና ት ለማካሄድ ያነሳሳኝ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ 2 ምዕራፍ ሁለት 2. ክለሳ ድርሳናት 2.1 የተዛ ማጅ ጥናቶች ቅኝት የተለያዩ ገፀባህሪያት አቀራረብ ሁኔታ የሚመረምሩ ጥናታዊ ጽሁፎችን ለመ መልከት ተሞክሯል ነገር ግን ትኩረታቸው በተ ለያዩ የአማርኛ ልቦለድ መፃህፍት ውስጥ በ ሚገኙ የ ውስጥ አርበኞች ገፀባህሪያት አ ቀራረብ ሁኔታ ላይ አድርገው የቀረቡ ጥናታዊ ፅሁፎች ለማግኘት አልተቻለም፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ርዕ ሰ ጉዳይ መሠረት ያደረጉ ጥናታዊ ፅሁፎች ባይኖሩም በተለያ ዩ የገፀባህሪ ያት ዓይነቶች ላይ የተሠሩ ጥናታዊ ፅሁፎ ች በመገኘታቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፤ እመቤት አብዱቅ ‹‹ የሙ ስለም ገፀባህሪያት አሳሳል በተመረጡ ረጅም ልቦለዶ ች ውስጥ ›› በ 1999 ዓ . ም ባቀረበችው ጥናት ሦስት ልቦለዶ ች ን ተመልክታለ ች ፡፡ እነሱም ጣምራ ጦር (1978) ፣ምሬት (1985) እና እሾሀማ ወርቅ (1992) ናቸው፡፡ የአጥኚዋ አላማ በተመረጡት ራጅም ልቦለዶች ውስጥ የሚገኙትን ሙስሊ ም ገፀባህ ሪያት አሳሳል አካላዊና ህሊናዊ መልኮች ከሃይማኖታዊ አስተም ህሮትና ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ተጨ ባጭ ሁኔታ ( ህይወት ) አንፃር ተንትኖ ማሳየት ነው፡፡ ጥናታዊ ፅሁፉ ከዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር የ ሚያመሳ ስ ለው በገፀባህሪያት አሳሳል ላይ ማተኮሩ እና በገበየሁ አየለ ‹‹ ጣምራ ጦር ›› ላይ መሠራቱ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ መጽሐፍ ላይ ቢሠራም ጥናቱ የተሠራው በልቦለዱ ውስጥ በሚገኙት ሙስሊም ገፀባህሪያት ላይ ነው፡፡ ትኩረቱም ከሙስሊምነታ ቸ ውና ከኢስላም ሥርዓት ጋር ገፀባህሪያቱ እንዴት እንደተሳሉ ማሳ የት ነው፡፡ ይህ ጥናት ደግሞ የ ሚያተኩረው በገፀባህሪያት አቀራረብ ላይ ሆኖ ከውስጥ አርበ ኝነታው አንፃር ነው፡፡ አ ሰ ፋ መኮንን በ 1997 ‹‹ የዩንቨርስቲ ገፀባህሪያት አቀራረፅ በ ወ ለፈንድ እና በየምሽት እንግዳ ›› የሚል የዲግሪ ማሟያ ፅሁፉን አቅርቧል፡፡ጥናቱ ሁለት ልቦለዶችን ተመርኩዞ የተሠራ ነው፡፡ እነሱም፡ - ወለፈንድ እና የምሽት እንግዳ ናቸው፡፡ አጥኚ ው አላማዬ ብሎ የገለፀው በሁለቱ ልቦለዶች ውስጥ የሚገኙ የዪንቨርሲቲ ገፀባህሪያት አቀራረፅ አካላዊና ህሊናዊ መልክ ማጥናት ነው፡፡ ጥናታዊ ፅሁፉ ከዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር የሚያመሳ ስ ለው በገፀባህሪያት ላይ በማተኮሩ ብቻ ነው፡፡ 3 እመቤት አብዲሳ በ 1993 ዓ . ም ‹‹ የአርቲስት ገፀባህሪያት አቀራረፅ በሦስት ልቦ ለደች ውስጥ ›› የሚል ጥናታዊ ጽሁፍ አቅ ርባለች፡፡ በጥናቷ ያካተተቻቸው መፃህፍት ራህማቶ፣ ህያው ፍቅር እና ጭምብል ናቸው፡፡ የአጥኚዋ አላማ በልቦለዶቹ ውስጥ ደ ራስዎ ቹ የተዋ ናይ ና ሰዓሊ ገፀባህሪያት አካላዊና ህሊናዊ መልክ ስለው ያቀረቡበት መንገድ ከ ገፀባህሪያት አሳሳል መሠረታዊ ባህሪያትና ከገፀባህሪያት ስብዕና ጋር በማነፃፀር ማሳየት ነው፡፡ይህ ጥናት ከዚህ ጥናት ጋር የሚያመሳስለው ገፀባህሪያት ላይ ተመርኩዞ በመሠራቱ ነው፡፡ ታምር ከበደ ‹‹ ጦርነት በአማርኛ ልቦለዶች ውስጥ ›› በ 1980 ዓ . ም ጦርነትን መሠረት አድረገው የተፃፉ ልቦለዶ ች ን አይ ቷል፡፡ ስለጦርነት ምንነትም አስረድቷል፡፡ የጦርነት መንስዔዎችን እና ዓይነቶችን ለማሳየት ሞክሯል፡፡ በጥናቱ ላይ ካተኮ ረባቸው መ ጽሐ ፍት አንዱ ጣም ራ ጦር ነው፡፡ ይህን መፅሀፍ በሀገሮች መካከል የ ሚደረግ ጦርነት ዓይነት መድቦታ ል ፡፡ ይህን ጥናት ከዚህ ጥ ናት ጋር የሚያዛምደው ( የሚያመሳስ ለው ) ጥናቱ ካ ቶከረባቸው መጽሐፍት አንዱ ጣምራ ጦር በመሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሱ ጥናት የሚ ያተ ኩረው በጦርነቱ መንስዔ እና ጦርነቱ በ ሚያስከትለው ውጤት ላይ ነው፡፡ በገፀባህሪያቱ አቀራረብ ሆነም ስለገፀባህሪያቱ ያነሳው ጉዳይ የለም፡፡ ከዚህ ጥናት ጋር የሚያዛ ምደው ቀጥተኛ ሆነ ነገር የለም፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የገለጽኳቸውም ሆኑ ሌሎች በተለያዩ የገፀባህሪያት ዓይነቶች የተሠሩ ጥናቶ ቢኖሩ ም ከዚህ ጥናት ጋር የሚያመሳስላቸው በገፀ ባህሪያት ላይ ተመስረተው በመሠራታቸው እንጂ ከዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ያላቸው ጥናታዊ ጽሁፎች አልተገኙም፡፡ 4 2.2 ንድፈ ሃሳባዊ ዳራ 2.2.1 የአርበኛ ምንነት አርበ ኛ ሀገሩን የሚወድ ለሀገሩ ስሜት ያለው ሰው ነው፡፡ ለሀገሩ ማንኛውንም መስዕዋት ለመክፈል ዝግጁ የ ሆነ ሰው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጥናትና ምር ምር ባዘጋጀው አማርኛ መ ዝገበ ቃላት አርበኛን እንዲህ ይገልፀዋል ‹‹ አርበኛ ለሀሩ ለወገኑ ክብርና ነፃነት ሲል በአገር ወዳድነት ከውጭ ወራሪ ጋር የተዋጋ ጀግና ›› / ገጽ 312 ፣ 1 993/ ከላይ እንደተገለፀው አርበኛ ለሀገሩ ለወገኑ ነፃነት በጀግ ንነት የሚወጋና የሀገሩን ክብርና ሉአላዊነት የማያስደፍር ነው፡፡ ለምሳሌ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም የአፍሪ ካ ሀገሮች በነጮች ቅኝ - ግ ዛት በወደቁበት ዘመን ሉአላዊነቷ ተከብሮ ሳትደፈር ያቆያት ጀግኖች አርበኞች በከ ፈሉት መስዕዋትና ትግል ነው፡፡ ያ ንን ዘመ ናዊ ጦር ያለዉንና የሰለጠ ነውን የፋሺስት ጣሊያንን ጦር ያሸነፉት በወኔና በሀገር ወዳድነታቸው፣በአልበገር ባይነታቸው እና ለሀገራቸው ካላ ቸው ፍቅር ነው፡፡ አርበኛ ቆ ራጥ፣ጀግና ነው፡፡ በሀገሩ ላይ ለሚመጣ ነገር ወደ ኋላ የማይል ነው፡፡ በሀገሩ ላይ እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ለማስወገድ በቆ ራጥነት በጀግንነት ይፋ ለማል፡፡ ደስታ ተክለ ወልድ አርበኛ ከግዕዝ ሐ ርብ ኪለው ቃል የመጣ መሆኑን ገልታ የአርበኛን ምንነት እንዲህ ብለዋል ‹‹ ጦረኛ፣የጦር ገበሬ፣ጨካኝ፣ ደፋር፣ ቆረጥ፣ጐበዝ ›› / ገጽ 954 ፣ 196 2/ ፡፡ ከዚህ ብያኔ የምንረዳው አርበኛ ጦርኛ ( ተዋጊ ) ደፋር ቆራጥ መሆኑን ነው፡፡ በተመሣሣይ መልኩ ኪዳነወልድ ክ ፍ ሌ ም አርበኛ የሚለው ቃል ከግዕዝ ሐረብ ከሚለው ቃል የመጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፤ አርበኛ የሚለውን ቃል ሲያብራሩም ‹‹ ሰይፋዊ ሰይፋም፣ ሰይ ፈኛ፣ተዋጊ / ገጽ 460 ፣ 19 4 8/ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከሁለቱ ከተሠጡት ከያኔዎች የምንረደው አ ር በ ኛ ተዋጊ መሆኑን ነው "Random House compact un Abridged dictionary" አርበኛን የገለፀው እንዲህ ነው "patriot a person who loves, supports a nd defend, his or her country and its interest with d evotion" ከዚህ የምንረዳው አርበኛ ሀገሩን የሚወድ ሀገሩን የ ሚደግፍና ከመጥፎ ነገሮች የሚከላከል መሆኑን ነው፡፡ አንድ ሰው ጦር ሜዳ ሆኖ ለሀገሩ ድንበር እና ለ ነፃነት ከመዋ ጋት በተጨማሪ ሀገሩን በጥሩ ጐን ካ ስጠራ እና ለሀገሩ ጥሩ ነገር ከሠራ አርበኛ ሊባል ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በምርምር አንድ ግኝት ካገኘ ከራሱ ስም በተጨማሪ የሀገሩንም ስም ያስ ጠራል፡፡ አንድ ስፖርተኛ ተወዳድ ሮ ሲያሸንፍ የሀገሩን ስም በጥሩ ጐን ያስጠራል፡፡ 5 ለምሳሌ አንድ አትሌት ሀገሩን ወክሎ በተወዳደረበት ውድድር ሲያሸንፍ የሀገሩን መዝሙር ሲያዘምርና ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርጐ ሲያሰቅል ለሀገሩ አርበኛ ሆነ ማለት ነው፡፡ በአጠቃላ ይ አርበኛ ለሀገሩ ፍቅር ያለውና ስለሀገሩ የተለየ ስሜት ያለው እንዲሁም ሀገሩን በጥሩ ጐን የሚያስጠራ እና የሀገሩን ነፃነት ለማስ ከበር የሚ ዋ ጋ ነው፡፡ 6 ምዕራፍ ሦስት 3. የውስጥ አርበኛ ገፀባህሪያት አቀራረብ በተመረጡ የአማርኛ ልቦለዶች 3.1 የረመጥ ልቦለድ የውስጥ አርበኞች ገፀባህሪያት አቀራረብ ረመጥ በ 1928 ቱ የፋሺስት ኢጣሊያ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ ታሪካዊ ልቦለድ ነው፡፡ ልቦለድ የሚያተኩረው በዚያን ወቅት በተፈፀሙ ድርጊቶች እና በሀገር ፍቅር ስሜት ተነሳስተው በትምህርት ዓለም ላይ እያ ሉ ጓደኞሞች የነበሩ ወጣቶች በኋላ ላ ይ ከሚቀላቀሏቸው ሀገር ወዳድና ነፃነት ናፋቂዎች ጋር በመሆን ምስጥራዊ ማህበር አቋቁመው ጠላ ትን ለማጥቃት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲያደርጉ እናያለን፡፡ እነዚህን የውስጥ አርበኞች ገፀባህሪያት በመቀጠል እንመለከታለን፡፡ ገብሬ ቦጋለ ገብሬ ጣለያኖች ኢትዮጵያ ን እንደወረሩ ማይጨው ድረስ ዘምቶ የነበረ እና በኋላም የኢትዮጵያ ሠራዊት ድል ተመቶ ሲበተን ወደ አደዲስ አበባ ተመለሰ፡፡ ጓደኞቹን ሰብስቦ አ ንድ ማህበር እንዲመሰርቱ ያደረገው እሱ ነው፡፡ ባለው የመጀመሪ እርዳታ ህክምና አ ስጣጥ እውቀት ጫካ ገብተው ወደ ሚዋ ጉት አርበኞች በመሄድ የህክምና እ ዳ ርታ የሚያደርግ እንዲሁም አዲስ አበባ ስ ለ ሚገኘው ወራሪ ኃይል መረጃ በማቀበልና እንዴት ጠላትን ማጥቃት እንዳለባቸው ከማህበሩ አባላት ጋር የወሰኑትን ለአርበኞች በማሳወቅ ከፍተኛ ሚና ያለውን የውስጥ አርበኝነት ሥራ ሰርቷል፡፡ ሁሴን ኢድሪ ስ ሁሴን በ ማህበሩ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ካላቸው አባላት መካከል አንዱ ነው፡፡ መኖሪያ ቤቱን ለመስብሰቢያነት እንዲገለግል ከማድረጉ በተጨማሪ ያለውን ሀብት በሙሉ ማህበራቸው የሀገር ነፃነትን ለማስገኘት ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲውል አድርጓል፡፡ ሁሴን ለማህበራቸው ካከናወናቸው ሥራዎች ውስጥ ለማህበሩ ይጠቅማሉ ሀገር ወዳድ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ሰዎች ወደ ማህበሩ እንዲገቡ እና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ማድረግ ነበር ፡፡ 7