ውክፔዲያ:የመጣጥፍ አቀማመጥ ልምድ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የውክፔዲያ መጣጥፍ አቀማመጥ ልምድን የሚያሳይ ስዕል

መጣጥፎች ይህን መሠረታዊ የአቀማመጥ ልምድ እንዲከተሉ ይመከራል። እነዚህ ልምዶች ለእርዳታና ለምክር የሚያገለግሉ እንጂ ጥብቅ የማይጣሱ ሕጎች አይደሉም።

የመጣጥፉ አርዕስት[ኮድ አርም]

አርዕስቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጣጥፉ ውስጥ ሲጻፍ፣ በ''' ''' ውስጥ ይቀመጥ። ለምሳሌ፦

  • «ሻይ ከልዩ የሻይ ቁጥቋጦ...» ሳይሆን «ሻይ ከልዩ የሻይ ቁጥቋጦ...»

የመጀመሪያው ዓረፍተ-ነገር[ኮድ አርም]

የመጀመሪያው ዓረፍተ-ነገር ስለ መጣጥፉ አርዕስት መሠረታዊ መረጃ ሊሰጥ ይገባል። ለምሳሌ፦

  • ስለ ድመት ያለው መጣጥፍ እንዲህ ይጀምራል፤ «ድመት አንስተኛ ስጋ በሊታ እንስሳ ስትሆን እቤት ውስጥ አይጥና የመሳሰሉትን ተውሳኮች ለመያዝ ታገለግላቸ።»

ከሌላ ቋንቋ የመጡ ቃላት[ኮድ አርም]

የመጣጥፉ አርዕስት የአማርኛ ቃል ካልሆነ፣ በቅንፍ ውስጥ የመነጨበትን ቋንቋ፣ ከዚያም ቃሉ በዚያ ቋንቋ አፃፃፍ፣ በመጨረሻም የቃሉ አባባል በአማርኛ በህዝባር (/ /) ውስጥ ያኑሩ። ለምሳሌ፦

  • ሩሲያ (መስኮብኛРоссия /ሮሲያ/) ወይም የሩሲያ ፌዴሬሽን (መስኮብኛ፦ Российская Федерация /ሮሲስካያ ፍየድየራትሲያ/) በአውሮፓ እና እስያ አህጉሮች ውስጥ የምትገኝ አገር ናት።

የውጭ ቃል ሆነው በአማርኛው ተናጋሪ ዘንድ ተለማጅነት ያላቸው ነገር ግን ትርጉማቸው በጣም ረጅም የሚሆን ከሆነ፣ በውጭውና በተለመደው ቃል ጽሁፍወን ያቅርቡ

የመረጃ መለጠፊያዎች[ኮድ አርም]

የመረጃ መለጠፊያዎች (ለምሳሌ የሀገር መረጃ) በቀኝ በኩል ይቀመጡ።

ስዕሎች[ኮድ አርም]

  • አብዛኛው ጊዜ በጣም ሰፊ ቦታ በመጣጥፉ ውስጥ እንዳይዙ፣ ለስዕሎች thumb የሚለውን ትዕዛዝ ይጠቀሙ። ለምሳሌ፦
[[ስዕል:Queen Nzinga 1657.png|thumb]]
  • በአንድ መጣጥፍ ውስጥ ብዙ ስዕሎች ካሉ፤ አቀማመጣቸውን በግራና በቀኝ ይለውጡ። left የሚለው ትዕዛዝ በግራ በኩል ያስቀምጣል። right የሚለው ደግሞ (ወይም ምንም የአቅጣጫ ትዕዛዝ ከሌለ) በቀኝ በኩል ያስቀምጣል። ለምሳሌ፦
[[ስዕል:Queen Nzinga 1657.png|thumb]]
[[ስዕል:Edgar Allan Poe 2.jpg|thumb|left]]
  • ለስዕል መግለጫ ይስጡ። ለምሳሌ፦
[[ስዕል:Queen Nzinga 1657.png|thumb|left|ንግሥት ንዚንጋ ከሏንዳ አስተዳዳሪ ጋር የሰላም ስምምነት ስታደርግ፣ 1657 እ.ኤ.አ.]]

ምንጮች[ኮድ አርም]

የግርጌ ማስታወሻዎች (እንግሊዝኛ፡ footnotes)፣ ዋቢ ምንጮች፣ ለተጨማሪ መረጃ የሚያገለግሉ መጻሕፍትና የውጭ መያያዣዎች ከመጣጥፉ ይዘት መጨረሻ ላይ በራሳቸው ንዑስ ክፍል ያስቀምጡ። የእነዚህ ምንጮች ቋንቋ አማርኛ ካልሆነ በቅንፍ () ውስጥ ቋንቋው ምን እንደሆነ ይጠቁሙ።

የግርጌ መለጠፊያዎች[ኮድ አርም]

የግርጌ መለጠፊያዎች ካሉ፣ ከምንጮች ዝርዝር ስር ይጨምሩ።

መዋቅር[ኮድ አርም]

መጣጥፉ መዋቅር ከሆነ የጠቅላላ ወይም የተወሰነ የመዋቅር መለጠፊያ ከግርጌ መለጠፊያዎች (ካሉ) ስር ይጨምሩ።

መደቦችና የሌሎች ቋንቋዎች መያያዣዎች[ኮድ አርም]

መደቦች ከመዋቅር መለጠፊያዎች (ካሉ) በታች ይቀመጡ። ተዛማጅ የሌሎች ቋንቋዎች መያያዣዎች ምርጥ ጽሁፍ (Featured article / Good article) ከሆኑ ከመደቦች በታች ያመልክቱ።