ኅዳር እጥነት

ከውክፔዲያ

ኅዳር ወር ፲፱፻፲፩ ዓ/ም የቸነፈር (ግሪፕ) በሽታ በአዲስ አበባ እና በሌላውም የኢትዮጵያ ግዛት ላይ ተነስቶ በመዲናዋ ብቻ ከአሥር ሺ በላይ ሰዎች ሞቱ።[1]። ይሄ በሽታ በዚያ ወቅት በዓለም ላይ ተሰራጭቶ የነበረው የ«እስፓኝ እንፍልዌንዛ» በመባል የሚታወቀው የጉንፋን 'ወረርሽኝ' ነው። በሽታውም «የኅዳር በሸታ» ተብሏል። ዛሬ በየዓመቱ «ኅዳር ሲታጠን» በሚል በየሰፈሩ ኅዳር ፲፪ ቀን የጽዳትና የቆሻሻ ማቃጠል ልማድ ይካሄዳል።

የከተማው ሰው ይህን ወቅት አስታኮ እንዲህ ብሎ ገጥሞም ነበር።

«መስከረም ሲጠባ ኅዳር ሲታጠን
ያኔ አሳይሻለሁ አረማመዴን»

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ «ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ»፣ ፩ኛ መጽሐፍ (፲፱፻፳፱ ዓ/ም) ገጽ ፴፱